ጀርመናዉያንን ስንቃኝ | ባህል | DW | 29.11.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ጀርመናዉያንን ስንቃኝ

ጦርነት ያደቀቀዉን ሀገራቸዉን ሃምሳ አመት ባልሞላ ግዜ ገንብተዉ፤ ወደ ዉጭ በሚልኩት ምርቶቻቸዉ Made in Germany በተሰኘዉ መለያቸዉ፤ በዓለም ዙርያ ታዋቂነትን እና ተወዳጅነትን አግኝተዋል።

ጀርመናዉያን ሀገራቸዉ በኢኮነሚዉ ከበለፀጉት ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያበቁት፤ ስራን በማክበራቸዉ እና ባለመናቃቸዉ መሆኑንም አስመስክረዋል። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን አመሻችሁ! በጀርመን ለረጅም ዓመታት የኖሩ ኢትዮጵያዉያን ስለ ጀርመን ስልጣኔ እና የጀርመን አገር ኑሮ ተሞክሮአቸዉን ያካፈሉበትን ጥንቅር ተከታይ ክፍል ይዘን ቀርበናል መልካም ቆይታ

አብዛኞች ጀርመናዉያን ስራን ከማክበርና ጠንክሮ ከመራት ባሻገር ከስራ መልስ ለሰዉነታቸዉ ጥንካሪና ጤናማ ኑሮ ትኩረት እንደሚሰጡ ይነገራል። በዚህም በዓለም ላይ ረጅም ዕድሜ ባለጸጎች መሆናቸዉ አንዳንድ ጥናታዊ መዘርዝሮች ይጠቁማሉ። ለረጅም ዓመታት በጀርመን ነዋሪ የሆኑት እና የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እዚህ በጀርመን ያጠናቀቁት የፖለቲካ ጉዳይ ምሁሩ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ፤ ጀርመናዉያን ስፖርትን እንደሚያዘወትሩ ይናገራሉ። በቦን ዩንቨርስቲ በእንስሳት ማዳቀል ስራ በረዳት ፕሮፊሰርነት መዕረግ በመምህርነት እና በምርምር ስራ ላይ የሚገኙት ፕሮፊሰር ዳዊት ተስፋዪ ጀርመናዉያን አዲስ ነገር ለማወቅ ጥረት ያደርጋሉ ባይ ናቸዉ።

አዲስ ነገር ከማወቅ ጋር በተያያዘ ጀርመናዉያን አለምን በመዞር የተለያዩ ቦታዎችን በማየት፤ የማህብረሰብን ባህል በመተዋወቅ ረገድ በዓለም ቀዳሚዉን ስፍራ መያዛቸዉ ይነገርላቸዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በህግ እና በፖለቲካ ሳይንስ እዚሁ ጀርመን ያጠናቀቁት ዶክተር ለማ ይፍራ ሸዋም ይንኑ ነዉ የሚናገሩት። በጀርመን ከ36 ዓመት በላይ የኖሩት እና ሁለት የአዛዉንቶች የጤና አገልግሎት ድርጅቶችን የሚያስተዳድሩት ወ/ሮ መሰረት አለፈለገሰላም ጀርመናዉያንን በሁለት መንገድ ነዉ የሚገልጹዋቸዉ። በሌላ በኩል ይላሉ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ በበኩላቸዉ ጀርመናዉያን የማህበረሰቡን የአካባቢዉን ስርዓት ለመጠበቅ ስርዓትን ያከብራሉ። በሌላ በኩል ይላሉ ዶክተር ለማ ጀርመናዉያን እስካሁን ድረስ ልለምደዉ ያልቻልኩት ባህልም አላቸዉ። ምግብ ቤት ዉስጥ ከተገባበዙ በኋላ ሁሉም የየራሱን ወጭ የመክፈሉን ባህል። ጀርመን በኢትዮጵያዉያን ዓይን በሚል ርዕስ የያዝነዉን ቅንብር ሙሉ ክፍል ያድምጡ !ለመሰናዶዉ መሳካት ቃለ መጠይቅ የሰጡንን በሙሉ እናመሰግናለን።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 29.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16sTW
 • ቀን 29.11.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16sTW