1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶ/ር ኢንጂኔር ዮሴፍ ገሰሰ፤ የታዳሽ ኃይል ምርት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሞያ በጀርመን

ሐሙስ፣ ነሐሴ 30 2016

«ከጀርመናዉያን ጋር ስራ ስትሰሪ ለመጀመርያ ጊዜ ይፈትናል ይከብዳል፤ ምክንያቱም ባህሪያቸዉን ማወቅ ያስፈልጋል። ጀርመኖች በጣም ቀዝቃዞች ናቸዉ። በመጀመርያ ያጠናሉ ሰዉን፤ ትንሽ ጊዜ ያያሉ፤ ከለመዱ እና ከተግባባህ በኋላ ግን ሁሉንም ነገር እየሰጡ በጣም ጠንከር ያለ ግንኙነት ያዳብራሉ። በጣም ደስ የሚለኝ ባህሪያቸዉ ነዉ»

https://p.dw.com/p/4kKL3
ዶ/ር ኢንጂኔር ዮሴፍ ገሰሰ፤ የታዳሽ ኃይል ምርት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሞያ በጀርመን
ዶ/ር ኢንጂኔር ዮሴፍ ገሰሰ፤ የታዳሽ ኃይል ምርት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሞያ በጀርመንምስል Privat

ዶ/ር ኢንጂኔር ዮሴፍ ገሰሰ፤ የታዳሽ ኃይል ምርት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሞያ በጀርመን

«ከጀርመናዉያን ጋር ስራ ስትሰሪ ለመጀመርያ ጊዜ ይፈትናል ይከብዳል፤ ምክንያቱም ባህሪያቸዉን ማወቅ ያስፈልጋል። ጀርመኖች በጣም ቀዝቃዞች ናቸዉ። በመጀመርያ ያጠናሉ ሰዉን፤ ትንሽ ጊዜ ያያሉ፤ ከለመዱ እና ከተግባባህ በኋላ ግን ሁሉንም ነገር እየሰጡ ለመደገፍ ለማገዝ ሲሞክሩ ይታያል። በጣም ጠንከር ያለ ግንኙነትም ያዳብራሉ። በጣም ደስ የሚለኝ  ባህሪያቸዉ ነዉ« ሲሉ የገለፁልን ኢንጂኔር ዶ/ር ዮሴፍ ገሰሰ ናቸዉ።

ዶ/ር ዮሴፍ ገሰሰ በጀርመን የምህድስና ትምህርትርታቸዉን አጠናቀዉ በጀርመን ብሎም ከተለያዩ ምዕራባዉያን ሃገራት ጋር በታዳሽ ኃይል ምንጭ አገልግሎት ከፍተኛ ተቋማት ዉስጥ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ዶክተር ዮሴፍ በኢትዮጵያም የማማከር አገልግሎትን በዘርፉ ለተሰማሩ ባልደረቦቻቸዉ ይሰጣሉ።  

በጀርመን ሲኖሩ ከ 15 ዓመታት በላይ የሆናቸዉ ዶ/ር ዮሴፍ ገሰሰ፤ በጀርመን በተለይ በንፋስ ታዳሽ ኃይል አመንጭ ተቋማት ዉስጥ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በተለይ በአሁኑ ወቅት የስራ ልምዳቸዉን ይዘዉ ሙሉ ጊዜያቸዉን በማማከር አገልግሎት ላይ ተሰማርተዉ እየሰሩ ነዉ። በአሁኑ ወቅት ይህንኑ ሞያቸዉን ለማጋራት ወደ ኢትዮጵያ አቅንተዋል። ዶ/ር ዩሴፍ ገሰሰ፤ ቀደም ሲል በጀነራል ዊንጌት የሞያ ስልጠናን አጠናቀዉ፤ በሩስያ በምህድንስና ሞያ ተመርቀዋል። ከዝያም በአዳማ ዩንቨርስቲ በምህርነት ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል። በጀርመን የካቶሊክ የውጭ አገር አገልግሎት በጀርመንና መጠርያዉ katolische auslandische dienst በኩል ዳግም የከፍተኛ ትምህርት እድልን አግኝተዉ በምህንድስና ሞያ የዶክትሪት ትምህርታቸዉን አጠናቀዋል። ዶ/ር ዩሴፍን በዶቼ ቬለ እንግዳ ለማድረግ ብዙ ጥረት ካደረግን ከረጅም ጊዜ በኋላ በስልክ አግኝተን ይመቸኛል ሲሉ ስለትህርት ጉዞዋቸዉ ስለሞያቸዉ አጫዉተዉናል።

የንፋስ ታዳሽ ሃይል
የንፋስ ታዳሽ ሃይል ምስል Christian Charisius/Pool/REUTERS

ዶ/ር ዮሴፍ ገሰሰ በጀርመን በምህንድስና ሞያ የዶክትሪት ማዕረጋቸዉን ከጀርመንዋ ዳርምሽታት ዩንቨርስቲ ካገኙ በኋላ በጀርመን ሁለተኛ፤ በአዉሮጳ ደግሞ አራተኛ በሆነዉ በብሪመን ባህር ወደብ ሥራ ተቀጥረዉ፤ በንፋስ ታዳሽ ኃይል ሞያ ዘርፍ ማገልገል ጀመሩ። እስከካሁን በመጣሁበት የትምህርት እና የግልጋሎት ዘመን በማስተማር እና በመማር ዘርፍ ተጠምጄ ስለቆየሁ አሁን ደግሞ በሞያዉ ላገልግል ብዬ የመስክ ሥራን ጀመርኩ ሲሉ አጫዉተዉናል።

ጀርመንን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም አገራት የኤሌክትሪክ ኃይልን በመጠቀም ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ ተስማሚ የአየር ንብረት እንዲኖር ከፍተኛ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስገባት የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም ረገድ ትኩረት ሰርታ እንደምትሰራ የሃገር ዉስጥ መገናኛ ብዙኃን ይናገራሉ።  

በዚህ ረገድ ዶ/ር ዮሴፍ ገሰሰ እንደሚሉት፤  ዩኒቨርሲቲዎች የኤሌትሪክ ኃይልን ለማመንጨት በዘርፉ የተማረ የሰው ኃይል ማምረት እና ማብቃት ያስፈልጋል ለዚህም የረጅም ጊዜ እና የአጫር ጊዜ ስልጠናን በመስጠት የሰዉ ኃይልን እዉቀትን ማስፈፋት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።   

ዶ/ር ኢንጂኔር ዮሴፍ ገሰሰ፤ የታዳሽ ኃይል ምርት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሞያ በጀርመን
ዶ/ር ኢንጂኔር ዮሴፍ ገሰሰ፤ የታዳሽ ኃይል ምርት አገልግሎት ከፍተኛ ባለሞያ በጀርመንምስል Privat

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና  ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ የግማሽ ቀን ስልጠና እና የእውቀት ልውውጥ ላይ ኢንጂኔር ዶ/ር ዮሴፍ ገሰሰ ተሳትፈዋል።

የዶ/ር ዮሴፍ የእዉቀት ልዉዉጥ ግብዣ የመጣዉ የጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ማህበር (GIZ) ባደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ምሁራንን በሃገር ውስጥ ልምድ እና እውቀታቸውን እንዲያካፍሉ በሚያደርጉበት ፕሮጀክት አማካኝነት በተዘጋጀ የእውቀት ልውውጥ መድረክ ነው፡፡ ዶ/ር ዮሴፍ በዩኒቨርሲቲው ለሚገኙ የሜካኒካል፤ ኤሌክትሪካል፤ ኤሌክትሮ ሜካኒካል መምህራን እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ስልጠና ሰጥዋል፡፡

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ