ዶክተር አምባቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆኑ | ኢትዮጵያ | DW | 09.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዶክተር አምባቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆኑ

ተሰናባቹ አቶ ገዱ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር የአማራ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር የቆየውን ትስስር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የአማራ እና የትግራይ ህዝብን አንድነት ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎችም እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:34

የአማራ ክልል መስተዳድር አዲስ ፕሬዝደንት ሾመ

ዶክተር አምባቸው መኮንን በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ። የአማራ ክልል ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባዔ ክልሉን ሲመሩ የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡትን የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ ዛሬ በምትካቸው ዶክተር አምባቸውን በርዕሰ መስተዳድርነት ሾሟል። ተሰናባቹ አቶ ገዱ ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር የአማራ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር የቆየውን ትስስር እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። የአማራ እና የትግራይ ህዝብን አንድነት ለማፍረስ የሚደረጉ ሙከራዎችም እንዲቆሙ ጠይቀዋል። አለምነው መኮንን ከባህርዳር ዝርዝሩን ልኮልናል። 
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ

Audios and videos on the topic