ዶክተር ብርሃኑና የፓርቲያቸዉ አመራሮች የትግል ርምጃ | ኢትዮጵያ | DW | 22.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዶክተር ብርሃኑና የፓርቲያቸዉ አመራሮች የትግል ርምጃ

ከአርበኞች ግንባር ጋር የተዋሀደዉ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋና እና የፓርቲያቸዉ ከፍተኛ የአመራር አባላት ወታደራዊ ትግል ለማካሄድ ወደሚንቀሳቀሱባት ኤርትራ ጠቅልለዉ መሄዳቸዉን አንድ የንቅናቄዉ አመራር አባል አስታወቁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:31
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:31 ደቂቃ

ዶክተር ብርሃኑና የፓርቲያቸዉ አመራሮች የትግል ርምጃ

ቁጥራቸዉ ይፋ ያልተደረገዉ የአርበኞች ግንቦስ ሰባት የአመራር አባላትን ይዘዉ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ወደኤርትራ ያመሩት ሌሎች አማራጮችን ጨምሮ በወታደራዊ ትግልና በሕዝባዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ገዢ ፓርቲ ለማስወገድ መሆኑን የንቅናቄዉ የአመራር አባል ተናግረዋል። ለንደን የሚኖሩት የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአመራር አባል ዶክተር ታደሰ ብሩ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት ዶክተር ብርሃኑ እና ጓዶቻቸዉ ትግሉ ወደሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች ያመራሉ። መጀመሪያ ኤርትራ ቢሄዱም ግማሾቹ ታጋዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ ስላሉ ወደኢትዮጵያም ገብተዉ ለታጋዮቹ አመራር እየሰጡ እንደሚታገሉ ገልጸዋል። ዝርዝሩን የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic