ዶክተር መረራ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው | ኢትዮጵያ | DW | 29.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዶክተር መረራ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ዶክተር መረራ ከጠበቆቻቸዉም ሆነ ከራሳቸዉ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸዉ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም መርማሪዎች የጀመርነዉ ምርመራ አልተጠናቀቀም በማለታቸዉ ፍርድ ቤቱ ለመጪዉ ጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:10 ደቂቃ

ዶክተር መረራ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

 
በዛሬዉ ዕለት በፌደራል  የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ የቀጠሮ ችሎት የቀረቡት የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ፕሬዝደንት እና  የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸዉ። ከጠበቆቻቸዉም ሆነ ከራሳቸዉ የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸዉ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም መርማሪዎች የጀመርነዉ ምርመራ አልተጠናቀቀም በማለታቸዉ ፍርድ ቤቱ ለመጪዉ ጥር 18 ቀጠሮ እንደሰጣቸዉ በስፍራዉ የተገኘዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ገልፆልናል። ስለፍርድ ቤት ዉሎዉ አዜብ ታደሰ ዮሐንስን ቀደም ብላ በስልክ አነጋግራዋለች። 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic