1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት እና የኤርትራ የፕሪስ ነጻነት

ዓርብ፣ መስከረም 8 2002

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ኤርትራ በአለም ከሚገኙ አገሮች ታላቁ የጋዜጠኞች እስር ቤት የሚገኝበት አገር ነዉ ሲል ገለጸ። ድርጅቱ ትናንት ከቀትር በኻላ ይፋ ባደረገዉ መግለጫዉ ከጎርጎረሳዉያኑ 2001 ጀምሮ ሰላሳ ያህል ጋዜጠኞች እና ሁለት የሚዲያ ሰራተኞች በእስራት ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/JjqK

እንደ ድርጅቱ ዘገባ በአለማችን ጋዜጠኞችን መብት በመንፈግ እና በማሰር በማንገላታት ኤርትራ ከኢራን እና ከቻይና ጋር የመጀመርያዉን ቦታን ይዛለች። ይህንኑ ዘገባ በመመርኮዝ አዜብ ታደሰ በድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳይ ተጠሪ ኦምብዋስ ፔየርን እና የኤርትራዉን የማስታወቅያ ሚኒስቴር አቶ አሊ አብዶን በስልክ አነጋግራ ይህንን ዘገባ አጠናቅራለች።

ልክ የዛሪ ስምንት አመት እንደ አዉሮጻዉያኑ መስከረም 18 ቀን 2001 አ.ም በእዝች እለት ነበር በኤርትራ የፕሪስ ነጻነት ያበቃለት። በዚህ ቀን ግል ጋዜጦች ተዘጉ እንዱሁም በርካታ ጋዜጠኞች ታሰሩ። ይህንኑ ቀን በማሰብ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ዛሪ በስምንተኛ አመቱ በእስር ቤት ታጉረዉ ስለሚገኙት ጋዜጠኞች ዘገባዉን ይፋ ያደረገዉ እንደዘገባዉ
የኤርትራ ሂሊና እስረኞች በአሳሪዎቻቸዉ የሚፈጸምባቸዉ ጭካኔ ሰለቦች ብቻ አይደሉም እልቅዩ የአገሪቱ የአለም አቀፍ ወዳጆች በሚባሉት ወገኖች ጭራሽ በመዘንጋታቸዉም ጭምር ድርብ በደል ደርሶባቸዋል። በዚህም ምክንያት የኤርትራ መንግስት ለአፍሪቃ አሳፋሪ ነዉ። ለድንበርየለሹ ዘገባ ኤርትራ ምን መልስ ይኖራት ይሆን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ
«በመጀመርያ ደረጃ ድርጅቱን ድንበር አያግዴ የጋዜጠኞች መብት ተቆቋሪ ድርጅት ሳይሆን የምለዉ፣ ድርበር አያግዴ የሰላዮች ድርጅት ነዉ። ደግሞ ለዚህ ረብ የለሽ ወሪ ምንም አይነት መልስ መስጠት አልፈልግም»
እንደ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በኤርትራ ባለፉት ስምንት አመታት እንደ አዉሮጻዉያኑ 2001, 2006 እንዲሁም የካቲት ወር 2009 አ.ም ላይ ጋዜጠኞች በጅምላ ወደ እስር ወርደዋል ነዉ።
በድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳይ ተጠሪ የሆኑት ኦምብዋስ ፔየር በዚህ ስምንት አመታት ዉስጥ በኤርትራ የታሰሩት ጋዜጠኞች ቁጥር እጅግ ጨምሮአል።
«በኤርትራ በአለም ጋዜጠኞችን በማንገላታት እና በማሰር ከሚታወቁት አለም አገሮች ቻይና እና ኢራን እኩል ሆናለች። በአሁኑ ወቅት በአለማችን በርካታ ጋዜጠኞች የታሰሩባት አገር በመሆን የመጀመርያዉን ቦታ ይዛለች»
እንደ ድርጅቱ የአፍሪቃ ተጠሪ ኦምብዋስ ፔየር ገለጻ ምንም እንኳ ኤርትራ ትንሽ አገር ሆና ብዙ ነገር በስፋት በአለም መድረክ ባይነገርም አገሪቷን በማስተዳደር ላይ ያለዉ አንባገነን መንግስት በአገሪቷ ለሚገኙ ጋዜጠኞች የመናገር መብት በመንፈግ ሚዲያዎችን በመዝጋት ጋዜጠኞች የሚሰቃዩባት አገር ነች። በርግጥ በኤርትራ የታሰሩት የጋዜጠኞች ቁጥር ስንት ደርሶ ይሆን የኤርትራዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አሊአብዶ
«ስንት ጋዜጠኞች ታሰሩ አልታሰሩ ይህን የአገሪቷ የሉአላዊነት ጉዳይ ነዉ። ማንም፣ ምን ሰራችሁ ምን እየሰራችሁ ነዉ ብሎ የመጠየቅ መብት የለዉም። ይህን በአገራችን ዉስጥ የምናየዉ የራሳችን ጉዳይ ነዉ።»
እንደ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት በኤርትራ ታስረዉ የሚገኙት ጋዜጠኞች በብረት ሳጥን በመሰለ ቤት ወይም በምድር ቤት ዉስጥ በሰሜናዊ ምዕራብ ኤርትራ በሚገኘዉ አዲ አቢቶ ወታደራዊ እስር ቤት ወይም ወደ ምፅዋ አቅጣቻ ላይ በሚገኘዉ ኢራይሮ እስር ቤት አልያም ደግሞ ዳህላክ ደሴት ላይ ባለዉ እስር ቤት ዉስጥ ተሰበጣጥረዉ እና ተዘግቶባቸዉ እንደሚገኙ
ዘገባዉ ይጠቁማል። እንደ አዉሮፓዉያኑ 2001 አ.ም ታስረዉ የነበሩ አራት ኤርትራዉያን ጋዜጠኞች ይህንን አስከፊ የእስር ሁኔታ መቋቋም እዳልቻሉም ይገልጻል። እንደ ድርጅቱ የአፍሪቃ ተጠሪ ገለጻ ምንም እንኳ ኤርትራ ትልቅ አገር ሆና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ባይኖራትም ይላሉ በአገሪትዋ ዉስጥ በጋዜጠኖች ላይ የሚደረገዉን ግፍ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በግልጽ እንድያዉቀዉ ነዉ ጥረታችን
«ምንም እንኳ ኤርትራ ትንሽ አገር ሆና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት እንብዛም ባይኖራትም ጥረታችን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሩን እንዲረዳዉ ለማድረግ ነዉ። ችግሩን ለመፍታት አንዳንንድ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም እስካሁን ምንም አይነት ዉጤት አላመጣንም። ለምሳሌ በአዉሮጻዉ ህብረት በአንዳንንድ ኤንባሲዎች በኩል ጥረት አድርገናል። በአስመራ ያለዉ የአገሪቷ አስተዳደር ጉዳይ ማለት ከፕሪዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ስለጋዜጠኞች ጉዳይ ምንም ጥያቄ ማቅረብ አልቻልንም። እሳቸዉም ምንም አይነት መልስ መስጠት አይሹም። የታሰሩትም ጋዜጠኞች ፍርድ እንዲያገኙ ቢጠየቅ እንቢ ብለዋል። ከእሳቸዉ ጋር ምንም አይነት ድርድር ማድረግ አልቻልንም።»
«እንደ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ በኤርትራ የፕሪስ ነጻነት አለ ነዉ። ነገር ግን ይላሉ አቶ አብዲ በፕሪስ ነጻነት ጀርባ ማህበረሰቡን ለመከፋፈል እና ከዉጭ ተወካዮች ጋር በማበር ወደ ተለያየ አቅጣጫ ለማምራት ለሚደረግ ጥረት በኛ በኩል ተቀባይነት አያገኝምም።»
በተጨማሪ ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ በኤርትራ በርካታ የሲቢል ሰራተኞች፣ የማስታወቅያ ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር እንዲሁም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦች የኢሜል የድብቅ ቁልፋቸዉን እንዲናገሩ መገደዳቸዉ መግለጫዉ አያይዞ ጠቅሶአል።

Issaias Afewerki, Präsident von Eritrea
ምስል picture-alliance /dpa