ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለፈጣሪ ምስጋና እንዲቀርብ ጥሪ የሚያቀርብ ዘለግ ያለ ደብዳቤ የተደበላለቀ ምላሽ አግኝቷል። በጥሪው ተስማምተው «አሜን» ያሉ የመኖራቸውን ያክል ሐይማኖት እና ፖለቲካ መደበላለቁ ያሳሰባቸው፤ አገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ያልተጣጣመላቸው ትችት ጽፈዋል። የአል ሸባብ ጥቃት እና የደራርቱ ቱሉ ጥሪም ውይይት ፈጥረዋል።
«የሠላም ድርድሩ በሰላም ተጀምሮ በሰላም ቢያልቅ ምኞታችን ነው። እውነት ለዚች አገርና ለሕዝቧ የሚያስቡ ከሆነ በሁለቱም ወገኖች መሐል ለሚነሱ አጀንዳዎች ሳይሆን እስከአሁን ለጠፋው የሰው ሕይወት እና ንብረት መውደም ብሎም ቅድሚያ ለሐገርና ለሕዝብ በመቆርቆር ከግትርነት ወጥተው ሁለቱም ወገኖች ለሠላም ብቻ ትግል ቢያደርጉ መልካም ነው።»
«ችግሩ ጋዜጠኛ ሙያዊ መሆኑን ለይቶ ማወቅን ይጠይቃል፡፡ ጋዜጠኛም ሀኪምም ካጠፋ በህግ ይጠየቃል፡፡ አሁን በህግ ለምን ተጠየቁ ነው ወይስ ሂደቱን እና አያያዙን ነው የምንተቸው፡፡ የአያያዙን ግልፅ አለመሆን ከሆነ ትክክለኛ የሆነ ጥያቄ ነው፡፡ መጠየቅ የለባቸውም ፤እኛ ነን የምናውቀው ከሆነ ግን ፍትህ እምን ይግባ? ማስተዋል!»
«ዉሳኔዉ በጣም ጥሩ ነው። ነገር ግን አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የቤት ባለቤቶች ጉዳይ በጣም ፍትህ አልባ ነው። ኩሽና የምትመስል ቤት አንድ ሺ ብር እያሉ በዚ ላይ የውኃ ክፈሉ የመብራት ክፈሉ እያሉ ደሀውን ያስጨንቃሉ። ምስኪኑ ህዝብ የት ሄዶ ይኑር ነዉ የምትሉት !? ....አከራዮች ሞት እንዳለ አትርሱ»