«ድርቅን ለመቋቋም በቂ ርዳታ አልተሰበሰበም» | ኢትዮጵያ | DW | 23.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

«ድርቅን ለመቋቋም በቂ ርዳታ አልተሰበሰበም»

በኢትዮጵያ አሳሳቢ የምግብ ዕጥረት ለገጠማቸው 10.2 ሚሊዮን ነዋሪዎች የተሰበሰበሰው የርዳታ ገንዘብ አነስተኛ መኾኑን አንድ ምግባረ-ሠናይ ድርጅት ዛሬ አስታወቀ።

ሕፃናት አድን (Save the Children) የተሰኘው ምግባረ-ሠናይ ድርጅት በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እስካሁን ያሰባሰበው የርዳታ ገንዘብ ከተጠበቀው፥ ከሲሶ በታች መኾኑን ዛሬ አስታውቋል። ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ከመንፈቅ ድረስ ለርዳታ የሚያስፈልግ ገንዘብ ነው ሲል ምግባረ-ሠናይ ድርጅቱ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ አቅዶ ነበር። ሆኖም እስካሁን ያሰባሰበው 30 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መኾኑን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ከ1977ቱ ድርቅ እጅግ የከፋው መኾኑን ባለሙያዎች ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በ1977 ዓ.ም. ጦርነትን የተከተለው አደገኛ ድርቅ ወደ ከፋ ረኃብ በመቀየሩ ወደ አንድ ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ማለቃቸው ይታወሳል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ