ድርቅና የምግብ እጥረት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 21.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ድርቅና የምግብ እጥረት በኢትዮጵያ

የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት /UNICEF/ በኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት ዉስጥ የሚዘነበዉ የበልግ ዝናብ በተለምዶዉ ከነበረዉ በታች ስለሚሆን በአጋሪቱ ያለዉን የድርቅ ሁኔታ ሊያባብስ እንደሚችል ትላንት ባወጣዉ ዘገባዉ ጠቅሰዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:39

የምግብ እጥረት

በደቡብ ሚስራቅ የአጋሪቱ ክፍል በአርቢቶ አደረነት የሚተዳደሩት በዝናቡ እጥረቱ ከፍተኛ ተጎጅ ልሆኑ እንደሚችሉ ዘገባዉ ጠቅሶ በሰብል ምርት ላይ ጥገኛ የሆኑ ክልሎችም በአማካይ ሊያገኙ የሚችሉትን ዝናብ እንደማያገኙ አመልክቷል።

የዝናብ እጥረቱ አሳሳቢ ነዉ የሚሉት በኢትዮጵያ የUNICEF ተወካይ ግልያን ሜልስኦፕ የምግብ፣ የዉሃና የጤና አገልግሎት የሚያስፈልጋቸዉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስከ ጥቅምት ወር 2010 ዓ/ም በጊዚያዊ መጠለያ ዉስጥ እንደሚቆዩ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ይህን ችግር ለመቋቋም UNICEF በበኩሉ ምን እያደረገ ይገኛል? 

ግልያን ሜልስኦፕ ስመልሱ፣«እኔ ራሴ አሁን በሶማሊ ክልል ነዉ ያለሁት። UNICEF ችግሩን ለመቋቋም የንፁህ ዉሃና የፅዳት አገልግሎት በማቅረብ፣ እንዲሁም መንግስት የከርስ ምድር ዉሃን የሚያወጣበት ፕሮጄክቶች ላይ ርዳታ በማድረግ የአዉራ ቦታ ይዘናል። ተመጣጣኝ ምግብ በማቅረብ በኩል በክፉኛ የተጎዱትን ህጻናት እየረዳን ነዉ። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ድርቁ ያጠቃቸዉ ቦታ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ቁጡሩ በከፍተኛ እየጨመረ መሆኑን ተመልክተናል። ስለዚህ ከመንግስት ጋር በመሆን በአፋርና በሶማሊ ክልል 49 ተንቀሳቃሽ የጤናና የተመጣጣኝ ምግብ የሚያቀርቡ ቡድኖች አሰማርተናል። እነዚህ ቡድኖች ለተፈናቀሉት አርቢቶ አደሮቹ የጤና አገልግሎት እየሰጡ ነዉ። የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ያጋጠማቸዉን ህጻናትም እያከሙ ይገኛሉ።»

የኢትዮጵያ መንግስት በጥር ወር 2009 ዓ/ም ይፋ ባደረገዉ ዘገባ እስካሁን 5,6 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ነበር። ከምግብ ርዳታ ፈላጊዎቹ 75 በመቶዉ በኦሮሚያ ክልል፣ በሶማሊ ክልልና በደቡብ ብሄር፣ ብሄሬሰብና ህዝቦች ክልል እንደሚገኙ UNICEF በዘገባዉ ጠቅሰዋል።

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሃራርጌ ዞን በኩርፋ ጫሌ፣ ሚዳጋና ፋድስ የተሰኙት ወረዳዎች ከፍተኛ የዝናብ እጥረት እንዳለና የቀንድ ከብቶች መኖ ስላጡ እየሞቱ እንደምገኙ ስማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ የአከባቢዉ ነዋሪ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። የምግብ እጥረት ላጋጠማቸዉ ሰዎች የሚሰጠዉ የሚግብ ርዳታ መጠን ንዑስ መሆኑን እኝህ ግለሰብ ተናግሮ «ለምግብ ርዳታ ፈላጊዎች ስንዴንና ዘይትን ጨምሮ መንግስት በየጊዜዉ ይሰጣቸዋል። የዝናብ እጥረት ስላለ አሁን ያለዉን መሬት ለእርሻ አመች አይደለም። ግን ዝናብ ሲዘንብ አንዳንዴ በአከባቢዉ ስንዴ ይመረታል። መንግስት ርዳታ ብያደርግም ብዙ ቁጥር ያላቸዉ ሰዎች ለችግር የተጋልጡት ሰዎች ብዙ በመሆናቸዉ ርዳታዉ በቂ ነዉ ማለት አልችልም» ስሉ ለዶይቼ ቬሌ አብራርተዋል። 

በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ ነዋር መሆናቸዉን የምናገሩት አቶ መሃመድ አሀመድ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በትላንትናዉ እለት ለኢትዮጵያ ሶማሊ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለድርቅ ተጎጅ ወገኖች 30 ከባድ የጭነት መኪኖች የእንስሳት መኖ እርዳታ ማበርከቱ ይናገራሉ።

የምግብም ሆነ የዝናብ እጥረት ጉዳዮችን በተመለከተ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት እና የምግብ ዋስትና ዘርፍ በኩል የበለጠ መረጃ ለማግኘት ያደርገነዉ ሙከራ አልተሳካም።

UNICEF በዘገባዉ 9,2 ሚልዮን ሰዎች የመጠት ዉሃና የፅዳት አገልግሎት እንደምያስፈልጋቸዉ ጠቅሶ እንዲሁም 303,000 ህጻናት በዚህ ዓመት ለአሳሳቢ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት እንደሚጋለጡ ዘገበዉ አመልክቷል። ይህን ችግር ለመቋቋም ድርጅቱ በጥር ወር 20009 ዓ/ም ተይቆ ከነበረዉ 110,5 ሚሊዮን ዶላርስ እስካሁን 14,8 ምሊዮን ዶላርስ መገኘቱም ዘገባዉ ጠቅሷል።

መርጋ ዮናስ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic