ድሬደዋ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት | ኢትዮጵያ | DW | 12.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ድሬደዋ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት አዲስ ምክትል ከንቲባ ሾመ። የከተማዋ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው የሁለተኛ የሥራ ዘመን አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመት ከመንፈቅ የድሬደዋ ከንቲባ ሆነው ያገለገሉት የአቶ ኢብራሂም ዑስማንን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ ነው ዛሬ አቶ መሀዲ ጊሬን በምክትል ከንቲባነት የመረጠው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

ምክትል ከንቲባ አቶ መሀዲ ጊሬ

የድሬደዋ አስተዳር ም//ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አስቸካይ ጉባዔው በፈቃደቸው የስልጣን መልቀቀያ ጥያቄ ያቀረቡትን የቀድሞ ከንቲባ ኢብራሂም ዑስማንን ጥያቄ ተቀብሎ አቶ መሀዲ ጊሬን በምክትል ከንቲባነት አስተዳደሩን እንዲመሩ መርጧቸዋል። በአስተዳደሩ የፖለቲካ ፣ የፀጥታ ችግሮችን እና ነዋሪውን ወደ አደባባይ እንዲወጣ ያስገደዱ ማነቆ ሆኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን መነሻ ያደረገ የሪፎርም ስራ ሲሰራ ቆይቷል። በፊደራል መንግሥት እና በአስሰተዳደሩ የተከናወነው የፖለቲካ ሪፎርም  አካል ተደርጎ የሚወሰድ ነው የዛሬው የአመራር ለውጥና ሽግሽግ። በዚህ ሂደት በዛሬው ዕለት በምክትል ከንቲባነት አስተዳደሩን እንዲመሩ የተሾሙት አቶ መሀዲ ጌሬ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡ ምክትል ከንቲባው የወጣቶችን ችግሮችን ለመፍታት ከወጣቱ ጋር በሰለጠነ አግባብ እንሰራለን ብለዋል ፡፡በምክር ቤቱ የስንብት ንግግር ደረጉት የቀድሞ የአስተዳደሩ ከንቲባ ኢብራሂም ዑስማን በብዙ ፈተናዎች ውስጥ የሚፈለገውን  ያክል ባይሆንም የሚቻለውን ለመስራት ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀው በአስተዳደሩ ማነቆ የሆነውን ቡድናዊ ትስስር በማስወገድ ሀዝቡን በማሳተፍ መስራት ከተቻለ ለውጥ ማምጣት ከባድ አይሆንም ብለዋል ፡፡

የቀድሞው ከንቲባ ኢብራሂም ስር የሰደደ የፍቅር እና አብሮ የመኖር አሴት እንዲሸረሸርና እንዲጠፋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው መጠራጠር እንዲጠፋ ሁሉም ነዋሪ ሊተብቀው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡የአስተዳደሩ ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ቀድሞ አፈ ጉባዔ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ከድር ጁሀርን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሲያደርግ አቶ አብደላ አህመድን የም/ቤቱ አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል ፡፡አቶ ሙሳ ጠሀ የአስተዳደሩ ፍትህ ፣ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ፣ አቶ አብዱሰላም አህመድ የግብርና ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ፣ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም ወ/ሮ ፋጡማ ሙስጠፋ የአስተዳደሩ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ መርጧል ፡፡በዕለቱ የም/ቤቱ ስብሰባ በሀላፊነት የተሾሙ አካለት ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በቃለ መሀላ አረጋግጠዋል ፡፡በአስተዳደሩ የተካሄደው የፖለቲካ ሪፎርም በሚፈለገው መልኩ ውጤት ስለማምጣቱ ቀጣዩ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል።

መሳይ ተክሉ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች