ድሬደዋ: በመጨው ምርጫ ለመሳተፍ 10 ፓርቲዎች እና 2 የግል እጩዎች ተመዘገቡ | ኢትዮጵያ | DW | 06.03.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ድሬደዋ: በመጨው ምርጫ ለመሳተፍ 10 ፓርቲዎች እና 2 የግል እጩዎች ተመዘገቡ

በመጪው ሰኔ በድሬደዋ ለሚካሄደው የፌደራል ህዝብ እንደራሴዎችና የከተማ ምክር ቤቶች ለመወዳደር 10 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች መመዝገባቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን እንደገለፁት በመጪው ሰኔ በድሬደዋ ለሚካሄደው የፌደራል እና የከተማ ምክር ቤቶች ህዝብ እንደራሴዎች ለመወዳደር 10 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ከሶስት መቶ በላይ ዕጩዎች ለሁለቱ ምክር ቤቶች በዕጩነት መቅረባቸውን የተናገሩት ኃላፊው ሁለት የግል ተወዳዳሪዎች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።
እጩዎችን ካስመዘገቡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ አቶ የሺጥላ ማሞ በምዝገባው መጨረሻ ምዕራፍ ችግሮች እንደነበሩ ጠቅሰው እጩዎቹ በተለያየ መንገድ ጫና ይደርስብናል በሚል ለመወዳደር መስጋታቸውን ግልፀዋል። በሌላ በኩል ፓርቲው ስራውን የሚያከናውንበት ፅ/ቤት እንዳይኖረው የተለየ ግልፅ ጫና እየተካሄደ ነው ብሏል፡፡ የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር ም/ቤት ባለው አ189 የምክር ቤት አባላት ብዛት በገዢው ፓርቲ በኩል ተመሳሳይ ቁጥር ያለው እጩ መመዝገቡ ታውቋል፡፡
በቀጣይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መርሀ ግብር መሰረት የመራጮች ምዝገባን ለማካሄድ የምዝገባ ጣቢያ ሰራተኞች ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መሳይ ተክሉ
ልደት አበበ
 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች