ድሬዝደን የዛሬ 75 ዓመት እና ዛሬ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 11.02.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ድሬዝደን የዛሬ 75 ዓመት እና ዛሬ

የዛሬ 75 ዓመት በተባበሩት ኃይሎች የቦምብ ውርጅብኝ የተንኮታኮተችው የጀርመኗ ድሬዝደን ከተማ ዛሬ አንሠራርታ ስትታይ ያንን ሁሉ ሰቆቃ ያለፈች አትመስልም። በወቅቱ በምሥራቅ ጀርመኗ ግዛት ድሬዝደን ከተማ ላይ የወረደው ቦምብ 25 ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ፈጅቶ፤ 25 ሺህ ገደማ ቤቶችን አውድሞ ከተማውን ወደፍርስራሽ ክምርነት መለወጡ ለታሪክ ተመዝግቧል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:25

አውሮጳ እና ጀርመን

የዛሬ 75 ዓመት በተባበሩት ኃይሎች የቦምብ ውርጅብኝ የተንኮታኮተችው የጀርመኗ ድሬዝደን ከተማ ዛሬ አንሠራርታ ስትታይ ያንን ሁሉ ሰቆቃ ያለፈች አትመስልም። ሆኖም ዛሬም ግን የጦርነቱ ጠባሳ በቀላሉ እንዳይዘነጋ ጥልቅ ማስታወሻ የተቀመጠባት በመሆኗ ያለፈ ታሪኳን የምታሳይበት ቤተመዘክር በከተማዋ ማዕከል ተሸክማለች። ያኔ የጦር እስረኛ የነበረው አሜሪካዊ ታሪክ ፀሐፊ ኩርት ቮንጉት «ስሎውተር ሃውስ ፋይቭ» በተሰኘው መጽሐፉ  ከቦምብ ድብደባው በኋላ የድሬዝደን ከተማ «የጨረቃን ገጸ ምድር መሰለ» ሲል የጻፈው አገላለጽ በብዙዎች ይጠቀስለታል። በእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ዘንድም ከፍተኛ ቃጠሎን ለመግለፅ «እንደ ድሬዝደን» የሚለውን አባባል መጠቀም የተለመደ መሆኑን የሚያስረዱ ሌሎች ጽሔፎችም አሉ። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በተቃረበበት በዚያን ወቅት በምሥራቅ ጀርመኗ ግዛት ድሬዝደን ከተማ ላይ የወረደው ቦምብ 25 ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ፈጅቶ፤ 25 ሺህ ገደማ ቤቶችንም አውድሞ ከተማውን ወደፍርስራሽ ክምርነት መለወጡ ለታሪክ ተመዝግቧል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች