ድሪደዋ ተረጋግታለች ተባለ | ኢትዮጵያ | DW | 28.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ድሪደዋ ተረጋግታለች ተባለ

በድሪደዋ ሰሞኑን ከተፈጠረው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት በሚል ከ250 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የከተማውን ሰላም ማስከበር ሀላፊነት የተረከበው የመከላከያ ፀጥታ ኮሚቴና ፀጥታ አካላት በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በተፈጠረው ተቃውሞ እና ሁከት ሳቢያ ተቃውሶ የነበረው የከተማዋ የሰላም ሁኔታ መረጋጋቱን ገልፃል።

 

በድሬደዋ መልካ ጀብዱ በሚባለው አካባቢ ተከሰተ በተባለ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። የፀጥታ አካሉ የሞቱ መንስዔ ከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑ ገልጿል።

በከተማው ሰሞኑን ከተፈጠረው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት በሚል ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የከተማውን ሰላም ማስከበር ሀላፊነት የተረከበው የመከላከያ ፀጥታ ኮሚቴ ከአስተዳደሩ የፀጥታ አካላት ጋር ትናንት አመሻሽ ላይ በጋራ በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በተፈጠረው ተቃውሞ እና ሁከት ሳቢያ ተቃውሶ የነበረው የከተማዋ የሰላም ሁኔታ መረጋጋቱን ገልፃል። ተዘግተው የነበሩ መንገዶች እንዲከፈቱ ከማድረግ በተጨማሪ የህብረተሰቡን የለት ተለት እንቅስቃሴ እንዲገታ አድርገው የነበሩ ሁኔታዎች መቆማቸውን ጠቅሰዋል። ህዝቡ ከሚያነሳው የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ውጭ የተቃውሞውን መንስዔ የሀይማኖት እና ብሄር መልክ በማስያዝ በከተማው ያለውን ሰላም ለማደፍረስ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን ያመለከተው መግለጫው ዓላማውን ለማክሸፍ ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።በህ/ሰብ ጥቆማ ፖሊስ መርማርሳ በተባለው አካባቢ በተካሄደ ፍተሻ  ሽጉጥና ክላሽንኮቭ መሳርያ መያዙንና ከዚህ ጋር በተያዙ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከትናንት በስቲያ በከተማው መልካ ጀብዱ በሚባለው አካባቢ ስለተከሰተው የሁለት ሰዎች ሞት ምክንያት ከ«DW» ለቀረበው ጥያቄ የፀጥታ ኮሚቴው የግለሰቦቹ ህይወት ያለፈው በአካባቢው ላይ ተከስቶ በነበረ ግጭት እንጂ ሰሞኑን ከተፈጠረው ሁከት ጋር የተያያዘ አይደለም ብሏል። በሌላ በኩል ሰሞኑን ከተፈጠረው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር የዋሉና አሁንም በመዋል ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ ደርሰዋል። የፀጥታ ኮሚቴው በቁጥጥር ስር እየዋሉ የሚገኙ ግለሰቦች የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ በማባባስና በመምራት በተለያየ አግባብ ተሳትፎ አላቸው  የተባሉ አካላት መሆናቸውን ገልፆ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን እና እንደ የጥፋት ተሳትፎአቸው እርምት ተሰጥቷቸው የሚለቀቁ መኖራቸውንና  በህግ መጠየቅ ያለባቸው በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ርምጃ ይወሰዳል ብሏል።

የፀጥታ ሀይሉ በቁጥጥር ስር እያዋላቸው ካሉ ግለሰቦች መካከል በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮች ይገኙበታል። " ማንም ይሁን ማን በድርጊቱ ተሳትፎ አለው የተባለ አካል ተይዞ ምርመራ በማድረግ ሊጠየቅ የሚገባው አካል በህግ እንዲጠየቅ ይደረጋል" ብሏል - ኮሚቴው በመግለጫው። ተጠርጣሪዎች ከህግ ውጭ በለሊት ጭምር እየተያዙ ስለመሆናቸው የሚነሳውን ጉዳይ መነሻ በማድረግ ከ«DW» ለቀረበው ጥያቄ ህግን በተከተለ አግባብ እየተሰራ መሆኑ ምላሽ ተሰቷል።

በአጠቃላይ የፀጥታ አካሉ በርካታ ወጣቶችንና ግለሰቦችን ለመያዝ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ ተቃውሞ ገጥሞታል ። በቁጥጥር ስር የዋሉ ልጆቻችን ይፈቱ የሚል ጥያቄ በመቅረብ ላይ ይገኛል።

መሳይ ተክሉ

አዜብ ታደሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች