ዴኒስ ጎልድበርግ-ደቡብ አፍሪቃዊዉ የመብት ታጋይ | አፍሪቃ | DW | 28.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዴኒስ ጎልድበርግ-ደቡብ አፍሪቃዊዉ የመብት ታጋይ

የአይሁድ ዝርያ ካላቸዉ ቤተሰብ የተወለዱት የኮሚንስት መርህ አራማጁ የአትላንቲክ ዉቅያኖስ ዳርቻን የሚያዋስነዉ ዘመናዊ የመኖርያ ህንጻዎች የሚገኙበት ኬፕታዉን አቅራብያ የሚገኘዉ የነጮች የመኖርያ ስፍራ ለሆነዉ ሆት ቤይ ነዋሪዎች ብርቅዬ ነዋሪ ናቸዉ። እኝህ ሰዉ እስከ ዛሪም ጃኮብ ዙማ ለሚያራምዱት ፓርቲ ደጋፊም ናቸዉ።

የሰማንያ ዓመቱ አዛዉንት በመኪና ማቆምያ ጋራዣቸዉ በር ላይ የጃኮብ ዙማ ደጋፊ መሆናቸዉን የሚያመለክት ማስታወቅያን የለጠፍኩ አንድዬ የአካባቢዉ ነዋሪ ነኝ ብለዉ ሲናገሩ በፈገግታ ነዉ- ሲል የዶቼ ቬለዉ ክላዉስ ሽቴከር ነጩን ደቡብ አፍሪቃዊ ዴኒስ ጎልድበርግን ይገልጻቸዋል፤ ዴኒስ ጎልድበርግ የደቡብ አፍሪቃዊዉ የነጻነት ታጋይ እና የሰዉ ልጆች መብት ተቆርቋሪ በመሆናቸዉ ይታወቃሉ።

View of Calella de Palafrugell, a smal fishers village of Costa Brava, Spain. Harbour

ፕሪቶርያ

ዴኒስ ጎልድበርግን ሰላሳ ዓመት ሲሆናቸዉ ነበር፤ ህይወታቸዉ አቅጣጫዉን ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ አቅጣጫ ፊቱን ያዞረዉ። ጎልድበርግ በዝያን ግዜ በደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ አራማጁ መንግስት፤ ከነጻነት ታጋዩ ከኔልሰን ማንዴላ እና ከ ሌሎች 15 የነፃነት ታጋዮች ጋር ታስረዋል፤ በጎርጎረሳዉያኑ 1964 ዓ,ም የክህደት እና የማጭበርበር የፍርድ ሂደት ተብሎ በሚታወቀዉ የሪቮና ፍርድ፤ በወንጀለኝነት ተፈርዶባቸዋል። በወላጆቻቸዉ ኩትኮታ እና አስገዳጅነት የህንጻ መሃንዲስ የሆኑት ደቡብ አፍሪቃዊዉ ጎልድበርግ፤ ያላቸዉ ዉስጣዊ ፍትሃዊነት ገና በለጋ እድሜያቸዉ ወደ ኮሚኒስቶች እና ወደ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲ «ANC» እንዲያመሩ አድርጓቸዋል። ዛሪም የቅምጥሎች መኖርያ ስፍራ በሆነዉ ኬፕታዉን አቅራብያ በሚገኘዉ ሆትቤይ ነዋሪ የሆኑት ጎልድበርግ ቅኑ ሃሳቢ፤ ጽኑ ህልመኛ፤ ታጋይና ምናልባትም ሩቅ ሃሳቢና ተመልካች ናቸዉ።

Bild: 31_Foto_Denis Goldberg_244x330.jpg Titel: GMF12 Foto Denis Goldberg Schlagworte: Global Media Forum 2012, Speaker31 Beschreibung: Speaker Denis Goldberg auf dem Global Media Forum 2012 Format: Sonderformat 244x330 Bildrechte: Denis Goldberg, Verwertungsrechte im Kontext des Global Media Forums 2012 eingeräumt.

ዴኒስ ጎልድበርግ

«የማርክሲዝምና የኮሚኒዝምን ርዕዮተ ዓለምን ለተከተለ እና ለገባዉ በካፒታሊዝም የሚቀርበዉ ሂስ ዛሪም እንዳለፉት ግዜያት ሁሉ ይታያል ብዪ አምናለሁ። በዓለም ዙርያ የሚታየዉ ግልጽ የሆነ ስግብግብነት፤ ደቡብ አፍሪቃንም ሲያጥለቀልቃት እያየሁ ነዉ። ይህ ስግብግብነት ድህነትን ማስታገስ ሳይሆን በማባባሱ ሀገሪቷን እያወደማት ነዉ። ይህ ደግሞ በድንገት የመጣ ሳይሆን፤ የባለሃብቶች እንቅስቃሴ ጽንሰ ሃሳብ ነዉ። የካፒታሊስት ባለሃብቶች በነጭም ሆነ በጥቁር ይመሩ፤ የሚያራምዱት በዚህ መልኩ ነዉ።»

በጎርጎረሳዉያኑ 1960 ዎቹ መጀመርያ፤ ANC ማለት የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲ ሰላማዊ ትግሉን ትቶ፤ በነጻነት ታጋዩ በኔልሰን ማዴላ መሪነት የትጥቅ ትግሉን ሲጀምር ጎልድበርግ አብረዉ ታግለዋል። የጎልድበርግ የህንጻ መሃንዲስነት ችሎታም ለፓርቲዉ ወታደራዊ ሃይል «ኡምኮኖ ዊ ስዝዊ» ጥቅም ሰቶአል። በትጥቅ ትግሉ ጎልድበርግ ቴክኒካዊ ክህሎት አማካሪ ሆነዉ ነበር ያገለገሉት። በጎርጎረሳዉያኑ 1963 ዓ,ም በአፓርታይድ አራማጆች ተይዘዉ ከታሰሩ በኋላ ቆየት ብሎ በአራት ግዜ ፍርድ እድሜ ይፍታህ ተፈርዶባቸዉ ወህኒ ወርደዋል። ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ለነጻነት ስቲታገሉ የነበሩት ጎልድበርግ እንደ ማንዴላ፤ በሮቢን ደሴት በሚገኘዉ ወህኔ ሳይሆን ለስር የተጋዙት፤ ነጭ በመሆናቸዉ፤ ነጭ በሚታሰርበት ወህኒ ወደ ፕሪቶርያ ወህኒ ነበር የተላኩት። ጎልድበርግ የእስር ግዜያቸዉን የተልኮ ትምህርት በመከታተል ተጠቅመዉበታል፤ አራት ግዜም በተለያየ ትምህርትን አጠናቀዋል። ጎልበርግ ከ22 ዓመት እስር በኋላ በ52 ዓመታቸዉ በጎርጎረሳዉያኑ 1985 ዓ,ም ከእስር ሲፈቱ፤ ለንደን ወደ ሚገኙት ባለቤታቸዉ ወደ ወ/ሮ ኤስመ ጋር ተሰደዱ። ከዝያም ለሚታገሉለት የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲ፤ ANC ን ፓርቲን ወክለዉ በ ተ,መ, ጽ/ቤት በኒዮርክ ስብሰባዎችን ተካፍለዋል። ጎልበርግ በለንደን ነዋሪ የሆኑት ባለቤታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩና በደቡብ አፍሪቃ የመጀመርያዉ የነጻ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ በጎርጎረሳዉያኑ 2002 ዓ,ም ወደ ደቡብ አፍሪቃ ይመለሳሉ። ወደ ደቡብ አፍሪቃም እንደተመለሱ በታንቦ ኢንቤኪ የስልጣን ዘመን ትርጉም የሌለዉ የፖለቲካ ስልጣንን አግኝተዉ የሀገሪቱ የዉሃና የደን ሃብት ሚንስትር በመሆን አገልግለዋል። ጎልድ በርግ ፖለቲከኛ ሆኖ ማገልገል የሚያስደስታቸዉ ተግባር ግን አልነበረም።

An aerial view of the Union Buildings in Pretoria where crowds and dignitaries have gathered for the inauguration of South Africas next president Jacob Zuma, South Africa, 09 May 2009. 21 heads of state are among the dignitaries witnessing the Inauguration of South Africas third democratically elected president, Jacob Zuma. EPA/JACOLINE PRINSLOO / POOL +++(c) dpa - Bildfunk+++

ፕሪቶርያ

«በእዉነቱ ፖለቲካ አንድ ትልቅ ሥነ-ጥበብ ነዉ። ስለዚህ ነዉ እዚያ ዉስጥ እጄን የማላስገባዉ፤ ምክንያቱም አልፈልግም። የኔ ሥራ የነበረዉ በፖለቲካ ለዉጥ ላይ እርዳታ መስጠት እንጂ፤ የፖለቲካ ሥራን ማግኘት አልነበረም። ምናልባት ያ የሥራዬ ወረታ ነዉ። ምናልባት ደግሞ እድለኛ ነበርኩ፤ ምክንያቱም ሁለቱም ሚስቶቼ በደንብ ተንከባክበዉኛል፤ በህይወት ዘመኔ ሁለት ግዜ አግብቼ ነበር። አልያ ደግም ምናልባት አንድ ሁለት አቋም ስላለኝ ይሆናል።»

በህይወት ዘመናቸዉ ሁለት ግዜ ትዳርን የያዙት ጎልድበርግ፤ አንደኛዋ ሚስታቸዉ ወ/ሮ ኤዝመ ጎልድበርግ እንደሳቸዉ ታጋይ የነበሩ እና በ22ዓመቱ የእስር ዘመናቸዉ ሁለት ግዜ ብቻ እንድያዩዋቸዉ የተፈቀዳለቸዉ ናቸዉ ፤ የምስራቅ ጀርመን ጋዜጠኛ የነበሩት ሌላዋ ሚስታቸዉ ደግሞ ብዙም ሳይቆዩ ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩቸዉ።

የነጻነት ታጋዩ ጎልድበርግ በህይወት ዘመናቸዉ ሁልግዜም ቢሆን ለማወቅ ጉጉት ያላቸዉ ለአላማቸዉ ጽኑ ሆነዉ ዘልቀዋል። ጎልበርግ አፓርታይድን ለመገርሰስ በተደረገዉ ትግል ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ፤ ህዝብ ሰላማዊ ኑሮ እንዲያገኝ ላበረከቱት ከፍተኛ ተግባር በጎርጎረሳዉያኑ 2009 ዓ,ም በፊደራል ጀርመን የሚሰጠዉን የክብር ሽልማት አግኝተዋል።

A supporter has the flag of South Africa painted on his face during the opening ceremony of the Confederations Cup soccer tournament at Ellis Park Stadium in Johannesburg, South Africa, Sunday, June 14, 2009. The tournament will run until June 28. (AP Photo/Martin Meissner)

ጎልበርግ በሀገራቸዉ በደቡብ አፍሪቃ እየታየ ያለዉ መንገዱን እየሳተ ስላለዉ የእድገት አቅጣጫ ስጋት ላይ ጥሎአቸዋል፤ በጣም እየረበሻቸዉ እንደሆነም ይናገራሉ። የደቡብ አፍሪቃ የትግል አብዮት ዉጤት ላይ ሳይሆን ገና መጀመርያዉ ምዕራፍ ላይ የቆመና፤ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲ የANC ፓርቲ ይህን ትግል ወይም አብዮት ዳር ማድረስ አይችልም የሚል ጥብቅ እና ጽኑ እምነት እንዳላቸዉ ጎልድበርግ ይናገራሉ።

«ANC በቀጣይ ለሁሉ እና ለየአንዳንዱ ማለት ለሁሉም ማህበረሰብ ሊሆን የሚችል ፓርቲ አይደለም። ይህ ማለት ለሰራተኛዉ፤ ለካፒታሊስቱ፣ ለባለመሪቱ፤ መሪት ለሌለዉ፣ ስራ ላለዉ ስራ ለሌለዉ ማለቱ ነዉ። መቼ እንደ ሆነ በርግጥ መናገር ባልችልም፤ ይፍጠንም ይዘግይ ANC መከፈሉ አይቀሪ ነዉ»እንደ ኮሚኒስት ርዕዮተ ዓለም አራማጅ እንደ ጎልድበርግ በደቡብ አፍሪቃ ማህበራዊ ፍትህን ለማምጣት ትክክለኛ ትግልን የሚያራምድ አንድ ግራክንፍ መኖር ይኖርበታል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን

Audios and videos on the topic