ዳግም ድል በለንደኑ ኦሎምፒክ | ኢትዮጵያ | DW | 11.08.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዳግም ድል በለንደኑ ኦሎምፒክ

ትናንት ምሽት በተካሄደው የለንደኑ ኦሎምፒክ የ5000 ሜትር የሩጫ ውድድር መሰረት ደፋር አሸናፊ በመሆን ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ወርቅ አስገኘች። የ10000 ሜትር የወርቅ ባለድሏ ጥሩነሽ ዲባባ በበኩሏ በትናንቱ ውድድር ሶስተኛ በመውጣት ለሐገሯ ተጨማሪ የነሐስ ሜዳይ አስገኝታለች።

ትናንት ምሽት በተካሄደው የለንደኑ ኦሎምፒክ የ5000 ሜትር የሩጫ ውድድር መሰረት ደፋር አሸናፊ በመሆን ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ወርቅ አስገኘች። የ10000 ሜትር የወርቅ ባለድሏ ጥሩነሽ ዲባባ በበኩሏ በትናንቱ ውድድር ሶስተኛ በመውጣት ለሐገሯ ተጨማሪ የነሐስ ሜዳይ አስገኝታለች። በከፍተኛ ሁኔታ ታሸንፋለች ተብላ የተጠበቀችው ኬንያዊቷ ተፎካካሪ ቪቪያን ቼሩዮት ውድድሩን በሁለተኝነት አጠናቃለች። በለንደኑ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እስካሁን ሶስት የወርቅ እና ሶስት የነሐስ ሜዳዮችን አስገኝተዋል። በሜዳይ ሰንጠረዡም ኢትዮጵያ ከዓለም በ22ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፤ ከአፍሪቃ 3 የወርቅ፣ 1 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳዮች ያላትን ደቡብ አፍሪቃ ተከትላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። የለንደኑ ኦሎምፒክ ከመጠናቀቁ በፊት ኢትዮጵያ ዛሬ እና ነገ የሚከናወኑ ሁለት ውድድሮች ይቀሯታል። የወንዶች 5000ሜትር ዛሬ ማታ 3 ሠዓት ተኩል ላይ ይከናወናል። ከዚያም ነገ ከቀኑ 7 ሠዓት ላይ የወንዶች የማራቶን ሩጫን በማካሄድ ኢትዮጵያውያን ውድድራቸውን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃሉ ማለት ነው። ትንናት አመሻሹ ላይ በለንደኑ ኦሎምፒክ በተካሄደዉ የ5ሽ ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ዉድድር፣ ስለተገኘዉ ዳግም ድል መሰረት ደፋር አስተያየትዋን ሰጥታለች። በለንደን ከምትገኘዉ ወኪላችን ከሃይማኖት ጥሩነህ ጋርም ስለ ዉድድሩ ሂደት ቃለ ምልልስ አድርገናል!

አዜብ ታደሰ

ሃይማኖት ጥሩነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 11.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15oCL
 • ቀን 11.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15oCL