ዳግም የጅምላ ጭፍጨፋ በቄሌም ወለጋ | ኢትዮጵያ | DW | 05.07.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዳግም የጅምላ ጭፍጨፋ በቄሌም ወለጋ

ኢትዮጵያ፤ ሌላ ሳምንት። ሌላ ጭፍጨፋ። ተመሳሳይ ሥፍራ፣ ተጨማሪ ሐዘን፣ ቁጣና ዉግዘት።ወለጋ-የደም አምባ።የትናንቱ ቄሌም ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ ፣ መንደር 20ና 21 ዉስጥ ነዉ። ከጭፍጨፋዉ ያመለጡ ነዋሪዎች እንደሚሉት በጥቃቱ ከ170 እስከ 300 የሚደርሱ በአብዛኛዉ የአማራ ተወላጆች በመደዳ ተገድለዋል።

«ከ170 - 300 የሚደርሱ ዜጎች በመደዳ ተገድለዋል» የዓይን እማኝ

በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ቀለም ወለጋ ዞን ሃዋ ገላን ወረዳ ለምለም ቀበሌ በታጣቂዎች ንጹሃን ዜጎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ የተመለከቱ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡ ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡት አስተያየት ሰጪ በየቤቱ በጅምላ ከተገደሉት ሌላ ታግተው በታጣቂዎች የተወሰዱም አሉ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የሰባት ሰፈራ ጣቢያ ነዋሪዎች አከባቢውን ለቀው መቻራ በተባለች የአከባቢው አነስተኛ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ የገለጹት አስተያየት ሰጪ ዛቻ እና ማስፈራሪያው “ኦነግ ሸነ” ካሉት የታጠቀ ቡድን ይደርሳቸው እንደነበር ገልጸዋልም፡፡ ግድያውም የአማራ ብሔር ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የአከባቢው ማህበረሰብ ሰፈራውን ለቀው በመውጣቱ ትናንት መከላከያ ደርሶ የሟቾች አስከረን ጠብቆ ማደሩን እና ዛሬ ሟቾችን በጅምላ መቃብር ከቀበሩ መካከል መሆናቸውን የገለጹት እኚው አስተያየት ሰጪ እስካሁን ከ170 በላይ መቀበራቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሌላው አስተያየት ሰጪ በፊናቸው የሟቾችን ቁጥር 300 ያደርሳሉ፡፡

 የመንግስት ኮሚዩኒለኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የተፈጸመውን የጅምላ ግድያ አረጋግጠው ለግድያውም መንግስት ሸነ በሚል በሽብርተኝነት የፈረጀውን የአ.ነ.ጦ. ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ለገሰ የጉዳት መጠኑም እየተጠራ ነው ብለዋል፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህምድ የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽመዋል ማለታቸውን ተከትሎ በቲዊተር ምላሽ የሰጡት የኦ.ነ.ጦ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ግድያውን የስርዓቱ ሚሊሾች የፈጸሙት ነው በማለት መንግስትን በተጠያቂነት ከሰዋል።።

 

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic