ዳግም የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት ስጋት | ጤና እና አካባቢ | DW | 11.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ዳግም የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት ስጋት

በዓለም አቀፍ ደረጃ የHIV ተሐዋሲን ስርጭት እስከ በጎርጎሪዮሳዊዉ 2030ዓ,ም ለመቀነስ እና ብሎም የኤድስ በሽታን ስጋትነን ለማብቃት ታቅዷል። የUNAIDS መረጃ እንደሚያሳየዉ በዚሁ የዘመን ቀመር 2015 መጨረሻ ድረስ በተሐዋሲዉ 36,7 ሚሊየን ሰዎች ተይዘዋል። እስካለፈዉ ሰኔ ወር ደግሞ 18,2 ሚሊየን ሰዎች የፀረ HIV መድኃኒት አግኝተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:36

በሽታዉን ለመከላከል የሚሠሩ ሥራዎች ተቀዛቅዘዋል፤

UNAIDS እንደሚለዉ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም ወዲህ አዲስ በተሐዋሲዉ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ብዙም ሲቀንስ አልታየም። በየዓመቱም 1,9 ሚሊየን ገደማ ሰዎች አዲስ በኤች አይቪ መያዛቸዉን ያመለክታል። በሌላ በኩል ላለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የኤች አይቪ ተሐዋሲ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ፤ አዲስ በበሽታዉ የሚያዙ ሰዎችም ቁጥርም እንዲሁ እየቀነሰ መምጣቱ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል። በቅርቡ ደግሞ በተሐዋሲዉ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተነግሯል። የበሽታዉን ስርጭት ለመከላከል ይደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸዉን የሚያመላክቱ አሉ። ሙሉ ቅንብሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች