ዳኞችና የኢትዮጵያ የፍትኅ ስርዓት | ኢትዮጵያ | DW | 10.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ዳኞችና የኢትዮጵያ የፍትኅ ስርዓት

የአዳዲስ ዳኞች ሹመት የፍርድ ሂደቶች እንዳይጓተቱ ይረዳል ተብሎ ቢታመንም በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ለሚታዩ መሠረታዊ ችግሮች ግን የሚያመጣው ለውጥ ሊኖር አይችልም የሚሉ ትችቶች እየቀረቡበት ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 28:11

ዳኞችና የኢትዮጵያ የፍትኅ ስርዓት

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ለፌደራል ፍርድቤቶች የ 111 አዳዲስ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል ። በዚሁ መሠረት ሁለት ዳኞችለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና እጩ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ፣ 34 ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም 75 ዳኞች ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ተሹመዋል ። ከ6 ዓመት ወዲህ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ዳኛ ሲሾም የአሁኑ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

የአዳዲስ ዳኞች ሹመት የፍርድ ሂደቶች እንዳይጓተቱ ይረዳል ተብሎ ቢታመንም በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ለሚታዩ መሠረታዊ ችግሮች ግን የሚያመጣው ለውጥ ሊኖር አይችልም የሚሉ ትችቶች እየቀረቡበት ነው ። የአሁኑ የዳኞች ሹመት ከከዚህ ቀደሞቹ ጋር ሲነፃጸር ግልፅነት የታየበት ነው ቢባልም ምልመላው እና ሹመቱ ከፖለቲካ ታማኝነት የፀዳ አይደለም ሲሉ የሚከራከሩ አሉ « ዳኞች እና የኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት» የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው ። የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉውን ውይይት ማድመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic