ዳንቴና ዲቪና ኮሜድያ | ባህል | DW | 12.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ዳንቴና ዲቪና ኮሜድያ

የጠላቶቹ አገዛዝ፥ የጣሉበት ቅጣት፥ የገጠመዉ መራር ሕይወት፥ ያን የአለም ምርጥ ቅኔዉን እንዲዘርፍ መዳልድል ሆነለት።-ዲቪና ኮሜዲያ።

ርግጥ በወጣትነቱም ገጣሚ ነበር።ከዚሕ ባለፍ ከአብዛኞቹ የኢጣሊያ በተለይም የሮማ ገዢዎች ቅሪቶችና የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የበላይነትን የሚፈልጉት ወገኖች የገጠሙት ግጭትና ዉጊያ እሁለት ከገመሳት የፍሎሬንስ ከተማ ወጣትች የሚለይበት ብዙም አልነበረም።ዱራንቴ ዴግሊ አሊጌሮ።ወይም ዳንቴ። ከጥንቷ የሮማ-ገዢዎች ዘር የሚወርሰዉ ያ ወጣት የቅዱስ ሮማ ሥርወ-መንግሥት ከተሰኘዉ ጎራ ተሠልፎ ሲዋጋ ቡድኑ ተሸንፎ-ከተማይቱ በጣሎቶቹ ተማረከች።

የጳጳሱ ታማኞች ይባሉ የነበሩት አሸናፊዎቹ ዳንቴ አምስት ሺሕ ፍሎሪን (የፍሎሬንሶች ገንዘብ) እንዲከፍል አለያም በእሳት ተቃጥሎ እንዲገደል ፈረዱበት።ከተወለደባት፥ከሚወዳት ከተማ እንደተለየ ቀረ።የጠላቶቹ አገዛዝ፥ የጣሉበት ቅጣት፥ የገጠመዉ መራር ሕይወት፥ ያን የአለም ምርጥ ቅኔዉን እንዲዘርፍ መዳልድል ሆነለት።-ዲቪና ኮሜዲያ።

ይሕ የሥነፅሁፍ በረከቱ ዳንቴን በወገኖቹ ዘንድ ኢል-ሶሞ ፖኤታ፥ ልዕለ-ገጣሚ ሲያሰኘዉ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ፔትሬርክና ከቦካሺዮ-ጋር ተደምሮ «የኢጣሊያ ሥነፅፍ-ዘዉዶች» የሚል አክብሮት አስችሮታል።ለዳንቴ ኢጣሊያ በተለይም ፍሎሬንስ ዉስጥ የተለያዩ መታሰቢያ ሐዉልቶች ቆመዉለታል።መንገዶች፥አብያተ-መዘክሮች በስሙ ተሰይመዉለታል።

እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር በ1300ዎቹ መጀመሪያ የተበየነበት ፍርድ የተነሳለት ግን ባለፈዉ አመት ሰኔ-ነበር።ያዉም የፍሎሬንስ ከተማ ምክር ቤት ከአንድ ሺሕ ስድስት አመት በፊት የተሰጠዉን ፍርድ ለመሻር በሰጠዉ ድምፅ ከሃያ-አራቱ የምክር ቤት እንደራሴዎች አምስቱ ተቃዉመዉት ነበር።

ዳንቴ በሕወቱ ኮሞዲያ ያለዉን መፅሐፉን የመጀሪያዉ የሕወት ታሪክ ፀሐፊዉ ቦካሺዮ-ዲቪና ያከለበትን ቅኔ የሮማዉ ወኪላችን ተኽለ-እግዚ ገብረየሱስ ባጭሩ ያወጋን።