«ዲጂታል» አብዮት ፤ በሃኖፈር ትርዒት | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 25.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

«ዲጂታል» አብዮት ፤ በሃኖፈር ትርዒት

በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደታወቁት እንደ E-BAY እና AMAZON ትልቁ የቻይና የ ONLINE ንግድ ድርጅት «አሊባባ» ባለቤት የሆኑት የጠነጠኑት ቻይናዊው ሀብታም ፤ ጃክ ማ ፤ ቀደም ባሉት ዘመናት የተከሠቱት የኢንዱስቴትሪ አብዮቶች፤ ሰዎች

ጉልበታቸው እንዳይደክም ተተኪ በመሆን ትልቅ ድርሻ ማበርከታቸው አይካድም ፤ ያሁኑ ዘመን ፤ በተለይም እ ጎ አ ከ 2012 ወዲህ ፣ ጀርመን 4ኛ ኢንዱስትሪ ያለችው የዲጂታል አብዮት ደግሞ የሰውን ልጅ የአእምሮ ጥንካሬ ነጻ የሚያወጣ ነው ። በቀጣዩ ዘመን ፣ ማሺኖች መናገር፤ ማሰብ አለባቸው፤ ይህን ሲያደርጉም ፣ በነዳጅ ዘይት ወይም ኤልክትሪክ ሳይሆን፤ በመረጃ ክምችት (Data) ይሆናል የሚደገፉት። ዓለም ን ቴክኖሎጂ አይለውጣትም ፣ ከቴክኖሎጂ በስተጀርባ ያለው የሰው ልጅ ብሩህ ሕልም ነው ለውጥ የሚያስገኘው » ሲሉ ተናግረዋል።

ጃክ ማ፤ ይህን ያሉት ከመጋቢት 6-11 ,2007 ዓ ም በሰሜን የጀርመን ከተማ በሐኖፈር በተካሄደው በዘንድሮው ዓመታዊ የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ የመረጃ ቴክኖሎጂና ቴሌኮሙዩኒኬሽን ማዕከል ትርዒት (CeBIT) ላይ ነው። ጠቃሚ አገልግሎት ሰጪና የቅንጦትም የሆነው የሥነ ቴክኒክ ውጤት በያይነቱ በ «ሰቢት» ትርዒት ላይ እ ጎ አ ከ 1986 ዓ ም አንስቶ በያመቱ በፀደይ ወር የሚቀርብበት ዓለም አቀፍ ዝግጅት የተለመደ ሆኗል። 17 አዳዲስ ተጨምረው፤

3,262 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተሳተፉበት ፤ 201,000 ተመልካቾች በጎበኙት የኮምፒዩተርና የዘመናዊ የመገናኛና የመዝናኛ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ትርዒት፣ ዘንድሮ የክብር እንግዳ በመሆን የተሳተፈች ቻይና ነበረች። 612 ኩባንያዎች ያሠለፈችው ቻይና ለውድድሩም ሆነ ለትርዒቱ ድምቀት እንደሰጠችው አስተናጋጂዎቹ ጀርመናውያን ገልጸዋል።

አሁን መላው ዓለም፣ 4ኛ ስለተሰኘው የኢንዱስትሪ አብዮት ሆኗል የሚነጋገረው። ስለኢንተርኔትና ዓለም በዲጂታል ስለተሣሠረችበት ሥነ -ቴክኒክ! የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ አብዮት በውሃ እንፋሎት ተሽከርካሪን ለምሳሌ ያህል ባቡርን ማንቀሳቀስ የተቻለበት ርምጃ ሲሆን፣ ሁለተኛው የኤልክትሪክ ጠቀሜታ ፤ ከዚያም በኋላ ነው ኮምፒዩተር የሚከተለው። እነዚህ ሁሉ አሁን ዓለም ለደረሰበት ፈጣን መገናኛና መገልገያ ታላቅ እመርታ ነው ያስገኙት። በዘንድሮው የሃኖፈር ዓለም አቀፍ የኮምፒዩተርና ረቂቅ የመገናኛ መሣሪያዎች ዐውደ ርእይ፣ ማምረቻ መሣሪያዎችን ረቂቅ ከሆኑና ካልሆኑ ምርቶች ጋር ሁሉንም በዲጂታል መረብ ማስተሣሰር የሚል ነው። በሃኖፈሩ ትርዓት፤ የመረጃ ቴክኖሎጂ፤ ቅርንጫፍ ድርጅት (ቢቲኮም) ፕሬዚዳንት ዲተር ኬምፕፍ መጪው ዘመን ማለፊያ ዕድል የሚያጋጥምበት ነው ባይ ናቸው።

«እንደሚመስለኝ ፣ በመደበኛው የኢንዱስትሪ ዘርፍም ቢሆን የዲጂታልን አጠቃቀም --እስካሁን በገባን መሠረት ፤ በሚያመረቃ ሁኔታ ተግባራዊ አድርገነዋል። የጀርመን አውቶሞቢልና የማሺን ሥራ ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉልላት ላይ ነው። ቀጣዩ ርምጃ እንግዲህ፤ 4ኛውን ኢንዱስትሪ ምዕራፍ ለማሳካት ማለትም በዲጂታል አሠራር የኢንዱስትሪ ምርቶችን ምርት ጥራት ባለው ሁኔታ ለማቅረብና በመጨረሻም በፍጥነት እንድናመርት የሚያስችለን ይሆናል።»

ከኢንዱስትሪው 4ኛ ምዕራፍ ለመድረስ የታየው እመርታ፣ የምርትን ጥራት ከፍተኛ ዓለም አቀ ፋዊ ደረጃ ለማሰጠት ሲሆን፤ የአዲሱ ደረጃ አመዳደብ ከተጀመረ ቆይቷል። ጀርመን ከፍተኛውን ደረጃ ለመያዝ በመፍጨርጨር ላይ ትገኛለች። መንግሥት በዚህ ረገድ ስለሚያጋጥሙ አደጋዎች ግንዛቤ የጨበጠ ሲሆን፤ በጥንቃቄ በዲጂታል ረገድ ተዓምራዊ የኤኮኖሚ ዕድገት እንዲገኝም ጥሪ አቅርቧል።

እርግጥ ይህ ብቻውን በቂ አይደለም። የጀርመን ማይክሮሶፍት ድርጅት ፣ ለጀርመን የኢንዱስትሪ ሚንስትር ባቀረበው ማስገንዘቢያ ላይ ፣ የተጠቀሰውን ተዓምራዊ ዕድገት እንዴት ማስመዝገብ እንደሚቻል አመላክቷል። ማይክሮሶፍት የጀርመን ቅርንጫፍ ኀላፊ ክላውስ ሮትካይ፣ ----

«የዲጂታል አሠራር በተናጠል መሥራት ለሚወዱ አይሆንም፤ ትከሻ ለትከሻ ተገደጋግፎ መከናወን ያለበት ጉዳይ ነው። ይኸው ትብብር፤ በእርግጥ፤ ሳይንስን፤ ኤኮኖሚን፣ ፖለቲካንና ሕብረተሰብን ማስተባበር መቻል ይኖርበታል። ጀርመን አዲስ ፈለግ ለመከተል በዝግጅት ላይ ናት፤ በአሁኑ ቅጽበት ግን በከፍተኛው መካከለኛ ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው። በግልጽ ለማስረዳት፣ ጥቂት መናገር በሰፊው ደግሞ በተግባር ላይ መሠማራት ነው የሚያሻን። ተፈላጊው አዳዲስ የፈጠራ ሐሳቦችን ፤ በገንቢ ተግባር ለመለወጥ፣ አዲስ የመነሣሣት ስሜት እንዲፈጠር ማብቃት በድፍረት በመሠማራት፤ ደረጃ አውጥቶ መንቀሳቀስ ነው የሚበጀው፤ ዘወትር ከመወያያት!»

አንዳንዱ ክርክር ፤ በተለይ እጅግ በዛ ያሉ ሰነዶችን አጠባበቅን የሚመለከተው መካሄዱ ተፈላጊ ይሆናል። ከኩባንያ ውጭ በሚገኝ የመረጃም ሆነ ሰነዶች ማከማቻ ቦታ ወይም የየግል ሰነዶችም ሆነ መረጃ መሥጢር ማከማቻ ማዕከልና የንግድ ምሥጢር የአጠባባቅ ይዞታ፣ በጥሞና መምከሩ የሚያጠያይቅ አይሆንም። SAP በሚል ምሕጻር የሚታወቀው ማለትም Systems, Applications and Products in Data የተሰኘው የጀርመን የ « ሶፍትዌር » ኩባናያ የሥነ ቴክኒክ ክፍል ኀላፊ፣ ክላውስ ሎይከርት እንዲህ ይላሉ።

«በዲጂታል አሠራር የሚታቀፍ ማንኛውም ነገር ይዋል ይደር በዚያው ሥርዓት መከናወኑ የማይቀር በመሆኑ፤ ቀደም አድርጎ ሥራ ላይ ማዋሉ ይመረጣል። በአገልግሎቱ የሚጠቀሙ፤ ማለፊያ አጋጣሚ ይኖራቸዋል። ባሁኑ ጊዜ በየዕለቱ እንደሚታየው፤ አውቶሞቢል ሆነ የወለል መጥረጊያ ማሺን፤ ቴክኖሎጂው፤ የተወሳሰበ ከሆነ አይሰምርም፤ ስለሆነም ለግል ጥቅምም ሆነ ለንግድ በተቻለ መጠን ቴክኖሎጂውን ለተጠቃሚው ቀላል ማድረጉ ነው የሚመረጠው።»

የቁሳቁሶችን ተግባራዊ ትሥሥር የሚመለከተው የኢንተርኔት አገልግሎት ፤ እዚህም ላይ የዕቃዎችና ረቂቅ መሣሪያዎች ፣ የተቀናጀ ተግባር ሲወሳ ፣ ሰዎችን ፤ እንስሳትን፣ መሣሪያዎችን ፤ ማሺኖችንም ሁሉ ያጠቃልላል፣ የሚያስፈልገው ዋና ጉዳይ እጅግ ፈጣን በሆነ መንገድ የሚገናኙበትን ሁኔታ መፍጠር ነው። በሃኖፈሩ ዐውደ ርእይ በ 5 G የወደፊቶቹን ተንቀሳቃሽ ስልኮች አገልግሎት ለሙከራ ያሳየ ትርዒት በቮዳፎን በኩል ቀርቦ ነበረ። ይህም ከአሁኑ ወቅት(LTE)ደረጃ ማለትም Long Term Evolution፣ በ 1000 ጊዜ የሚበልጥ ነው። የጀርመን ቴሌኮምም፤ የዕድገት ተዓምር 4ኛ ምዕራፍ ለተሰኘው፤ የኤኮኖሚ ዕድገት፣ ትልሙን በዐውደ ርእዩ ላይ አቅርቦ ነበር። የቴሌኮም ዋና ሥራ አስኪያጅ ቲም ሆኧትገስ ፣

« በመጀመሪያ ጠንካራ የሆነው ሠር መሠረት ያለው ኢንዱስትሪ ሊጠቀስ ይችላል ከሶፍትዌር ጋር ተያይዞ! ከዚያ ቀጥሎ ነው፤ የተለያዩ የአጠቃቀም ሥርዓቶችን በማሥተሣሰር ረገድ፣ ስለዲጂታል አሠራር ደረጃንን ጠብቆ ፈር እንዲይዝ ስለማድረግም መነጋገር የሚቻለው። ሂደቱ ፣ ግሥጋሤው፣ ቅርብ ጊዜ ነው የጀመረው። ወደፊት ገሥግሠናል።፤ ወደ ኋላም ቀርተናል፤ እንዲህ ነው ብሎ ቁርጥ ያለ ቃል ለመናገር አስቸጋሪ ነው ። ይህን ሥነ ቴክኒክ በንግድ አርአያነት ያለው ለማድረግ፤ እርግጥ እጅግ ተስማሚ ቅድመ ግዴታዎች አሉ። »ሶፍትዌር AG የተሰኘው ኩባንያ ኀላፊ ካርል ሃይንትዝ ሽትራይቪኽ ተግዳሮቱ ቀላል ባይሆንም፤ የጀርመን ግሥጋሴ በዚህ ረገድ የሠመረ እንደሚሆን ነው የገለጡት። ለዚህ የሰጡት ምክንያትም ጀርመን የታወቀች በኢንዱስትሪ የገሠገሠች ሃገር በመሆኗ ለወደፊቱ አዲስ የሥነ ቴክኒክ እመርታ እጅግ ተስማሚ መሠረት አላት የሚል ነው።

በጎርጎሪዮሳዊው አዲስ ዓመት የወር መባቻ ውስጥ ላስ ቬጋስ ፤ ዩናይትድ ስቴትስ የተጠቃሚዎች የኤሌክትሮኒክስ ትርዒት Consumer Electronics Show (CES) በተሰኘው ዐውደ ርእይ ፣ የተጀመረው የአዳዲስ የረቂቅ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ----

በዚህ በአውሮፓ ም ፣ ባርሴሎና እስፓኝ ውስጥ፤ ከየካቲት 23-26 Mobile World Congress በተሰኘው ተመሳሳይ ትርዒት ቀጥሎ ፤ በጀርመን ፤ ሓኖፈር ከተማ ውስጥ ከመጋቢት 6-11 ,2007 CEBIT በሚል ምሕጻረ ቃል በሚታወቀው ዓመታዊ ግዙፍ የኤልክትሮኒክስ ዐውደ ርእይ ተደምድሟል። በላስ ቬጋስና በባርሴሎና ብቻ ሳይሆን በሃኖፈሩ ዐውደ ርእይም በእንግሊዝኛ Wearables የሚባሉት ረቂቅ ዘርፈ ብዙ ጠቃሚ ቀርበው ነበር። እዚህ ላይ wearable computer የሚሰኘው፤ ለስፖርተኛ እንደ አሠልጣኝ፣ ለሕመምተኛ እንደ ነርስ በመሆን ፤ የልብ ትርታን ፣ የደም ግፊትን፤ የንፁህ የሚተነፈስ አየር ኦክስጂን መጠንን ይህንና የመሳሰለውን በመለካት አገልግሎት መስጠት የሚችል «ዲጂታል» መሣሪያ ነው። የዓይን መንጽር ተንቀሳቃሽ ምስልና የመሳሰለው የሚታይበት ኢምንት የቴሌቭዥን ሣጥን ሆኖም የሚያገለግል ነው። ገላ ላይ የሚያርፍ ልብስም ኢምንት የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ታክሎበት ተጨማሪ የተለያየ ተግባር ያከናውናል፤ የሙዚቃ ማድመጫም ሆኖ ያገለግላል።

በሥነ ቴክኒክ መራቀቁ ፤ አንዳንድ ሁኔታዎች ቅንጦት ይምሰሉ እንጂ በዘመኑ ለሚከሠቱ የተለያዩ ችግሮች መፍትኄ የማቅረቡ ፉክክርና ትብብር የሚደነቅ ነው።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic