ዲያስፖራውና የመረጃ ምንጮቹ | ባህል | DW | 15.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ዲያስፖራውና የመረጃ ምንጮቹ

ለረዥም ጊዜ ዉጭ አገር የኖሩ ሰዎች፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት ወደ አገር ቤት መልዕክቶችን ለመላክም ሆነ ለመቀበል ወይም አገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ለመከታተል አስቸጋሪ እንደነበር ይናገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 08:24

የመረጃ ምንጮቹ

ዛሬ ለቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና እነዚህ ችግሮች ተቃለዋል። የበቤተሰብና የዘመድን ናፍቆት ለመወጣት ከስልክ መደዋወል አልፎ በskype ወይም viber በተባለዉ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች በምስል የተደገፈ ግኑኝነት ማድረግ ተችሏል። በኢትዮጵያ ይህን መሰሉን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የሚያስችል መሰረተ ልማት ገና በእንጭጩ ያለ ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሃገር ውስጥ ካሉ ቤተሰቦቻቸዉ፣ ዘመዶቻቸው ወይም ጓደኛቸዉ ጋር በእነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይገናኛሉ፣ ከዛም አልፎ የአገሪቱ የፖለቲካ፣ የእኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮችም በኢንተርኔት facebook, twitter, skype እና በviber እንደሚከታተሉ ይናገራሉ።


ጉዳቱ አዱኛ ትባላለች። ወደ ጀርመን የመጣችዉ በጎርጎሮሳዊው 1997 ነው። የሕጻናት ሃኪም ናት። በፍራንክፉርት ከተማ አካባቢ ነው የምትሠራው። ወደ ጀርመን እንደመጣች ከቤተሰብም ሆነ ከዘመድ ጋር የምትገናኘዉ በስልክ እንደነበረ ያኔ ኔትዎርኩም አስቸጋር እንደነበረ ትናገራለች። ግን አሁን ነገሮች ስለ ተሻሻሉ በአካልም ሆነ በኢንቴርኔትም ሁኔታዎችን እንደምትከታተል ትናገራለች። ከቤተሴብ እና ከዘመድ ግንኙነት አልፎ ስለ አገሪቱ ጉዳይ እንዴት መረጃ እንደምታገኝና፣ የትኛዎቹን ጉዳዮች እንደምትከታተል ጠይቀናት ነበር።

«እዛ ከሄድኩ ልጆችን እጠይቃለሁ። በአብዛኛዉ አሁን በኢንቴርኔት ነው የምከታተለው። በስልክ ብዙ ነገሮች አይወራም፣ ስለዚህ ለጊዜዉ ኢንቴርኔት ነዉ የምጠቀመዉ። እኔ በአሁኑ ሰዓት የአገሪቱን ጉዳይ አትኩሬ የምከታተለዉም ማስተር ፕላኑን በተመለከተ አገር ዉስጥ ያለዉን ረብሻ፣ ልጆችን ማሳደድ፣ ገበሬ ከመሬቱ መፈናቀሉ እና በልጆቹ ላይ እየተካሄደ ያለዉን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ነዉ።»


ሚልዮን ጌትነት ከኢትዮጵያ ወደ ጀርመን የመጠዉ ከሦስት ዓመት በፊት ነው ። በአሁኑ ሰዓት የዶክትሬት ትምህርቱን በDevelopment Geographyወይም የልማት ጆግራፊ በቦን ዩኒቨርሲቲ እየተማረ መሆኑን ይናገራል። እሱም በበኩሉ ወደ ጀርመን እንደመጣ ቤተሰቡም ሆኑ ዘመዶቹ ጋር የሚገናኘው በስልክ እንደነበረ ጠቅሶ አሁን ደግሞ ቫይርንና ዋትስ ኣፕን እንደሚጠቀም ይናገራል። ማህበራዊ ብዙኃን መገናኛ፣ ማለትም ፌስቦክና ትዊቴር ጨምሮ ሌሎች መገናኛዎች በትንሹም ቢሆን ውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዋነኛ የመረጃ ምንጭ እየሆኑ ነው። በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ አማካይነት መንግሥት የሚያከናውናቸውን ተግባራት ከመንግስት ምዲያዎች እንደሚከታተልም ሚልዮን ያብራራል። ሙያው ከልማት እና ግብርና ጋር የተገናኘ ስለሆነ በአገሪቱ ዉስጥ የሚሰሩት የልማት ስራዎች ላይ መረጃ ከመንግስት ሚዲያዎች እንደሚከታተል ከግል ብዙኃን መገናኛዎችም ደግሞ ከመብት ተሟጋቾች በኩል የሚሰጡትን መረጃዎች እንደሚያገኝ ይናገራል። ሚሊዮን ከመረጃዎች የተወሰኑትን ጠቅሷል

ጉደቱም በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ በማስትር ፕላኑ ላይ ስለሚካሄደው ተቀዉሞ የተሰማትንና መፍትሄ የምትለውን ተናግራለች ፣ «ለልማት ተብሎ አውሮጳውያን የሚለግሱትን ርዳታ እና የሚያፈሱትን መዓለ ንዋይ አገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ተረድተው ማቆም አለባቸው። ሌላዉ ደግሞ የዉጭም ሆነ የአገር ዉስጥ ጋዝጤኞች ፍቃድ አግኝተው በዚህ ጉዳይ ላይ መዘገብ እንዲችሉ መደረግ አለበት።»


አገር ዉስጥ ያሉት ሚድያዎችም ሆነ የዉጭዎቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ አለመሆናችዉን የፖለቲካ ተቋምችም ሆነ ግለሰቦች ሰይጠቅሱ አላለፉም። ጉደቱም ይህንኑ አንስታለች «ከጥቂት ብዙኃን መገናኛ ዉጭ አብዛኛዎቹ ጉዳዩን በደምብ በግልፅ ትኩረት ሰጥተው እየዘገቡ አይደለም። ለምሳሌ ፌስ ቡክ ላይ ከሚወጣው ዉጭ ፣ስለ ታሰሩት ወይም ስለ ሞቱት ሰዎች ቁጥር በግልፅ እየተዘገበ አይደለም ። አሁን ጀርመን አገር ያሉት መገናኛ ብዙኃን ጋዜጦችና ከዶቼ ቬሌ ዘገባዎች ዉጭ በቴሌቭዥን ሲዘግቡ አይቼ አላዉቅም።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic