ደቡብ አፍሪቃ፤ አል በሽር ሃገሪቱን እንዳይለቁ | አፍሪቃ | DW | 14.06.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ደቡብ አፍሪቃ፤ አል በሽር ሃገሪቱን እንዳይለቁ

አንድ የደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤት ትናንት ደቡብ አፍሪቃ የገቡት የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦመር አል በሽር አገሪቷን ጥለዉ መዉጣት አይችሉም ሲል ወሰነ። ፍርድ ቤቱ ይህን የአስቸኳይ ጊዜ ዉሳኔ ያስተላለፈው አንድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ተቋም ባደረገበት ጫና መሆኑ ታዉቋል።

አል በሽር ከአገር እንዳይወጡ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔዉን መራዘሙን የደቡብ አፍሪቃ የብዙኃን መገናኛዎች በመዘገብ ላይ ናቸዉ። የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ፓርቲ « ANC» በበኩሉ «ICC» ጥቅም የሌለዉ ተቋም ነዉ ሲል ዉሳኔዉን አስተባብሏል። ፕሬዚዳንት ኦመር አል በሽር በቁጥጥር ስር የመዋል ጥርጣሪ እያለባቸዉ ነዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ ላይ ለመገኘት ትናንት ወደ ደቡብ አፍሪቃ ያቀኑት።

Internationaler Strafgerichtshof mit Logo

አል በሽር በጦር ወንጀለኝነት እና በጅምላ ጭፍጨፋ ሰብዓዊ ፍጡር ላይ ከፍተኛ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት «ICC» በጎርጎረሳዉያኑ 2009 እና 2010 አል በሽር እንዲያዙ የማሰርያ ትዕዛዝ መቁረጡ ይታወቃል። በደቡብ አፍሪቃ ፕሪቶርያ ፍርድ ቤት የሚገኙ አንድ ዳኛ ባሳለፉት ዉሳኔ ለረጅም ጊዜ የተወሰነዉ የማሰርያ ማዘዣ አዲስ ዉሳኔ እስኪያገኝ ኧል በሽር ደቡብ አፍሪቃን ለቀዉ መጓዝ አይችሉም። ደቡብ አፍሪቃ የዓለም አቀፉ የጦር ወንደለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አባል በመሆንዋ፤ የተላለፈዉን የማሰርያ ትዕዛዝ ተፈፃሚ የማድረግ ግዴታ አለባት። በልማት ላይ የሚመክረዉና ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ የጀመረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት በICC መያዝ አለመያዝ ወሬ ተጋርዶአል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

ተዛማጅ ዘገባዎች