ደቡብ ሱዳን ወደ ጦርነት አዘቅት ትገባ ይሆን?  | አፍሪቃ | DW | 07.11.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ደቡብ ሱዳን ወደ ጦርነት አዘቅት ትገባ ይሆን? 

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር እና የእስካሁኑ አማፂ ቡድን መሪ ሪያክ ማቻር ከዚሕ ቀደም የተፈራረሙትን የሰላም ዉል ገቢር በማድረግ የአንድነት መንግሥት መመስረት ቁርጠኝነት ባለማሳየታቸዉ ሃገሪቱ እጦርነት አፋፍ ላይ መሆንዋ እየተነገረ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:22

ቋሚ ኮሚቶው የሚኒስቴሩን የሦስት ወራት ስራ ገምግሞአል

ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ባለፈው መስከረም ወር ባካሄዱት ውይይት መሠረት ማቻር ወደ አንድነት መንግሥቱ የፊታችን ኅዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲገቡ ከስምምነት ተደርሶ የነበረ ቢሆንም ባለፉት ሳምንታት ዉስጥ  የደቡብ ሱዳን መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ አካል ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የሰላም ውሉን ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻሉ የአንድነት መንግሥት ምሥረታው እንዲዘገይ መጠየቁ ይታወሳል። የአማፂው ወገን መሪ ሪየክ ማቻር ቃል አቀባይ ባለፈዉ ሳምንት ባቀረቡት ጥያቄ፤ ማቻር የአንድነት መንግሥት ምሥረታው ለስድስት ወራት እንዲዘገይ ጠይቀዋል ነበር ያለዉ። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር በበኩላቸዉ ማቻር ላቀረቡት የይራዘም ጥያቄ በቀጥታ ምላሽ ባይሰጡም፣ በተጠቀሰው ቀን ሁሉም ወገኖች የአንድነት መንግሥቱን ለመመሥረት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዉ ነበር። ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች የስልጣን ዉዝግብ ከገቡበት ከዛሬ አምስት ዓመት ጀምሮ በደቡብ ሱዳን በተቀሰቀሰ የእርስ በርስ ጦርነት እስካሁን ወደ 400 ሺህ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ሞተዋል። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አዘጋጅቶታል። በእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ የተዘፈቀችዉ ደቡብ ሱዳን ወደ ባሰ የጦርነት አዘቅት እየተንሸራተተች ነዉ ሲል  በዓለም አቀፍ ደረጃ የግጭትና ቀዉስን መነሻ የሚያጠናዉ ድርጅት «ኢንተርናሽናል ክራይስ ግሩፕ» ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ዓለም አቀፉ የቀዉስ እና ግጭት አጥኚ ቡድን ይህን መግለጫ ያወጣዉ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ቡድን የአንድነት ምስረታ ቀጠሮዉን ማራዘሙን ተከትሎ ነዉ። 


ገበያዉ ንጉሴ 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሃመድ 
 

Audios and videos on the topic