ደቡብ ሱዳን እና የሽግግር መንግሥት ምሥረታ | አፍሪቃ | DW | 21.08.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ደቡብ ሱዳን እና የሽግግር መንግሥት ምሥረታ

የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት አተገባበር ለመመልከት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው ስብስባ ላይ የኢጋድ ሚኒስትሮች ጉባኤ ሊቀ መንበር እንደተናገሩት የተኩስ አቁሙ መተግበር እርዳታ ለማዳረስም አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል። ስብሰባው የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት እና ባጋጠሙ ፈተናዎች ላይም ተነጋግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:55

ደቡብ ሱዳን እና የሽግግር መንግሥት ምሥረታ

በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ መከበሩ በመቀጠሉ ሃገሪቱ መረጋጋቷን መመልከቱን የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን በምህጻሩ ኢጋድ አስታወቀ። የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት አተገባበር ለመመልከት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው ስብስባ ላይ የኢጋድ ሚኒስትሮች ጉባኤ ሊቀ መንበር እንደተናገሩት የተኩስ አቁሙ መተግበር እርዳታ ለማዳረስም አመቺ ሁኔታ ፈጥሯል። ስብሰባው የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት እና ባጋጠሙ ፈተናዎች ላይም ተነጋግሯል። የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሥት ምሥረታ በየ6 ወሩ ሲራዘም ነበር። በመጨረሻ የተራዘመው የምስረታ ጊዜም የፊታችን ህዳር ያበቃል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ አለው።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic