ደቡብ ሱዳን እና ሰላም የማስፈኑ ዕድል | አፍሪቃ | DW | 05.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ደቡብ ሱዳን እና ሰላም የማስፈኑ ዕድል

በሚቀጥሉት ቀናት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የቀድሞው ምክትላቸዉ ሪይክ ማቻር የሰላም ውይይት ለማካሄድ እና ለወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም ይገናኙ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የደቡብ ሱዳን ጉብኚት ለደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ጫና ይዞ ነው የመጣው። በደቡብ ሱዳን የሰላም መስፈኑን ዕድል አስመልክቶ በስፍራው የሚገኙት የዶይቸ ቬለ ዘጋቢዎች የአድሪያን ክሪሽ እና ያን ፊሊፕን ዘገባ ልደት አበበ እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የደቡብ ሱዳን ጉብኚት አጭር እና ያልተጠበቀ ነበር። ኬሪ ላለፉት አምስት ወራት በርስ በርስ ጦርነት የደቀቀችው ስለ አዲሲቱ አፍሪቃዊት ሀገር የሚሰማቸውን ስጋት በቦታው ተነኝተው ነበር ለመግለፅ የወሰኑት ። ኬሪም ከፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ጋ ካደረጉት የአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ ባደረጉት ንግግር ቃላት አላጠራቸውም፤« በደቡብ ሱዳን የሚፈለገው ያለውን የዘር ማጥፋት ማስቆም ብቻ ነው» ሲሉ ተሰምተዋል። ምንም እንኳን በሀገሪቱ የተረጋጋ ነገር ባይኖርም ከቤተ መንግሥቱ ብዙም ራቅ ሳይል በጁባ ዮንቨርስቲ ትምህርት መሰጠቱ እንደቀጠለ ነው። ተማሪዎቹ የኬሪን ጉብኝት ከፍተኛ ግምት ሰጥተው ነው የተከታተሉት። በዚሁ ከፍተኛ ተቋም ተማሪ የሆነችው እስቴፈኒ በምዕራባውያን ርዳታ ከዚህ የከፋ ነገር እንዳይፈፀም መከላከል ይቻላል የሚል ዕምነት አላት።

« እድገት እና የአዕምሮ መረጋጋት እንድናገኝ።መሪዎቻችንን የምንለምነው ረጋ እንዲሉ እና ሰላም እንዲፈጥሩ ነው። ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ እንደ ተማሪ በሀገሪቱ ከፊል አካባቢዎች እና ጓደኛችን ላይ የሚደርሰውን እያየን ትምህርታችንን በአግባቡ ልንከታተል አልቻልንም።»

በዚሁ የከፍተኛ ተቋም የደቡብ ሱዳን የግጭት ጥናት ምሁር እና መምህር የሆኑት ሲሞን ሚኖጃ ግን ወቅታዊውን ግጭት የምዕራቡ ሀገራት ይፈቱታል ብለው አያምኑም። ሚኖጃ አዲሲቲቷ አፍሪቃዊት ሀገር ከሶስት አመት ገደማ በፊት ስትመሰረት የነበረውን ከልክ ያለፈ ደስታ ያስታውሳሉ። መምህር ሲሞን ሳይቀሩ ከሚኖሩበት ካርቱም ለቀው ነው ወደ አዲሲቷ መዲና ጁባ የገቡት። በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታትም ይሁኑ የተለያዩ የምዕራባውያን የልማት ድርጅቶች « ደቡብ ሱዳን» ን በተቻላቸው መጠን ለማሳደግ ትልቅ አላማ ይዘው ነበር የተነሱት፤ ነገር ግን እንደ ሲሞን ይህ ተግባራዊ ሲሆን አልታየም።

« ሰዎች ከተባለው ጥረት ምንም ያገኙት መሻሻል የለም። ከጁባ ጥቂት ኪሎ ሜትር ራቅ ብላችሁ ብትሄዱ የዚህን ጥረት ውጤት አትመለከቱም። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ሰዎች ተስፋ ቆራጥነት የሚታይባቸው።»

ይላሉ የግጭት ጥናት ምህሩ። ከባለፈው ታህሳስ ወር መጀመሪያዎቹ አንስቶ በደቡብ ሱዳን በፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና በቀድሞው ምክትላቸዉ ሪይክ ማቻር ደጋፊዎች መካከል አመፅ ሲነሳ ግን ተስፋ ያደረጉት ምዕራባዊያን ሳይቀሩ የተጀመረው ፕሮጀክት እውን እንደማይሆን ግልፅ ሆኖላቸዋል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ በጎሳዎች መካከል የሚታየው ግፅት በደቡብ ሱዳን አልተገታም። የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ተልኮ ሰራተኛ የሆኑ አንድ ሰራተኛ ራሳቸውን ሳይጠቅሱ እንደተናገሩት የሰለባዎቹ ክብደት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በዚህም የተነሳ የሲቪሉን ማህበረሰብ ማስጠንቀቅ የሆነው ተልኮዋቸውን እንዳይወጡ ከብዷቸዋል። ይህም በዘፍቃድ በቁጥጥር ስር ማዋል እና በሰላይ ድርጅቶች መደመጥ ጥቂቶቹ ናቸው። የደቡብ ሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ፊሊፕ አጉር ለዶይቸ ቬለ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የአለም አቀፉ ጦር ለራሱም አልሆነ፤

«ራስህን መከላከል ካልቻልክ በርግጠኝነት ለህዝቡም ልትከላከል አትችልም። ከለላ የሚሰጡዋቸውም ሰዎች በተባበሩት መንግስታት ተልኮ ስር ነበር። ስለሆነም ህዝቡ በጥሩ ሁኔታ እንደሚወጡ ትልቅ ተስፋ ነበረው ። እኔ ግን አሁን በቃ አከትሟል ነው የምለው።»

ምንም እንኳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ከጠቅላይ ሚኒስትር ኬሪ ጋ በነበራቸው ቆይታ ሳልቫኪር የሰላም ንግግር ለማካሄድ ቢስማሙም፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያል ቤንጃሚን ከዶይቸ ቬለ ጋር በየነራቸው ቃለ መጠይቅ እምብዛም ፍላጎት አላሳዩም።

«በርግጥ ደቡብ ሱዳን የምትሻው ርዳታ ነው እንጂ ማዕቀብ ወይንም ግምታዊነት አይደለም። »

ይልቁንስ እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሆነ የደቡብ ሱዳን ዋናው ችግር በአማፂያኑ በኩል የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። ይህ በመሆኑም የታቀደው የሰላም ውይይት መካሄዱ እና መተግበሩ አጠራጣሪ ነው።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic