«ደስታ»፣ ባህል ገላጭ ልብ-ወለድ በእንግሊዝኛ | ባህል | DW | 31.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

«ደስታ»፣ ባህል ገላጭ ልብ-ወለድ በእንግሊዝኛ

የኢትዮጽያ ገጽታ የኢትዮጽያዉያንን ባህል ሳይቀንስ ሳያጋንን በግልጽ ያስቀመጠ በተለይ ለዉጭዉ አለም የኢትዮጽያን አሳየ የተባበለት መጽሃፍ ባለፈዉ የአዉሮጻዉያኑ 2010አ.ም መጨረሻ ላይ ከምዕራባዉያኑ እጅ ገብቶአል።

ኢትዮጽያዊ ባህልን ገላጭ ልብ-ወለድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ

«በኢትዪጽያዉያን ላይ የሚታየዉን የኖረ ስር የሰደደ የአገራችንን ባህል፣ የጨዋን ባህል ግልጽ አድርጎ ያሳያል። በቤተሰቡ ያሉ ልጆች በምን አይነት ሁኔታ እንደሚነጋገሩ እና እንደሚገናኙ፣ ለአባታቸዉ ለእናታቸዉ፣ ብሎም በአካባቢዉ በጎረቤት በሰፈር በመንደር ላሉ አዛዉንቶች ያላቸዉን አክብሮት ሁሉ ግሩም አድርጎ አስቀምጦአል። በአገራችን የባላገሩን የስራ ወዳድነት ባህል፣ በልጆቹም እያደገ፣ እየጎለበተ ሲሄድ ይታያል። እናት ለልጆችዋ ያላትን ስሜት ግሩም አድርጎ ይተነትናል። አባት ለልጆቹ ለባለቤቱ ለሌሎችም ያለዉን ስሜት በአገራችን ባህል ጥርት አድርጎ ይጎነጉናል። ይህን መጽሃፍ የሚያነብ ሁሉ ለኢትዮጽያዊ ታላቅ አክብሮት ያድርበታል» ሲሉ መጸሃፉን ያነበቡ ኢትዮጽያዉያን ይመሰክራሉ። መጽሃፉ እጃቸዉ ገብቶ የማንበብ እድል ያገኙ ኢትዮጽያዉያን ስለመጽሃፉ እንዲህ ሲገልጹ አብዛኞቹ ምዕራባዉያ ደግሞ በመጽሃፍ የሰፈረዉ ታሪክ በፊልም መልክ እንዲቀርብ ይጠይቃሉ። የመጽሃፉ ደራሲ በበኩላቸዉ ታሪኩ በፊልም መልክ መቀረጹ ቆየት ብሎ፣ መጽሃፉ እራሱ በአማረኛ ቢተረጎም እና ለኢትዮጽያዊ ወገናቸዉ ቢደስር ምኞታቸዉ እንደሆነ ይገልጻሉ። በቅርቡ በአሜሪካን አገር ለአንባብያን የቀረበዉ በእዉነት ላይ የተመረኮዘዉ ልብ-ወለድ ደስታ ይስኛል መጠርያዉ። ደስታ መጽሃፍ በአማረኛ ተተርጉሞ በኢትዮጽያ ለአንባብያን እስኪ ደርስ የእንግሊዘኛዉን እትም ማግኘት ለምትሹ በድረ-ገጽ Desta and King Solomon’s Coin of Magic and Fortune በሚል ይገኛል። አዜብ ታደሰ የመጽሃፉን ደራሲ አቶ ጌቲ አንባዉን፣ መጽሃፉን ከአነበቡት ኢትዮጽያዉያን መካከል በአሜሪካን አገር በፕሮፊሰር ማዕረግ በመምህርነት ያገለገሉት የታሪክ ተመራማሪዉ ዶክተር አሉላ ዋሴን፣ በሰሜን አሜሪካ በአንድ ኮሌጅ ምክትል ፕሪዝደንት የሆኑትን ዶክተር ወርቁ ነጋሽን እና አቶ ጌታቸዉ አድማሱን አነጋግራለች። ሙሉ ጥንቅሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ