ደም አፋሳሹ የኬንያ ምርጫ | አፍሪቃ | DW | 02.01.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ደም አፋሳሹ የኬንያ ምርጫ

ኬንያ ዉስጥ በተካሄደዉ ፕሪዝደንታዊ ምርጫ ኪባኪ ዳግም አገሪቷን እንዲመሩ በምርጫ አሸንፈዋል ከተባለ ወዲህ በተነሳዉ አመጽ ደም አፋሳሹ ብጥብጥ እያሻቀበ ነዉ። በተቀናቃኝ ወገኖች ዘንድ የተነሳዉን ብጥ ለማርገብ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝና ጥይት በመጠቀሙ የሟቾች ቁጥር ጨምሮአል

የ 2008 ን የዘመን መለወጫ በእሳት

የ 2008 ን የዘመን መለወጫ በእሳት

መንግስት በአገሪቱ መገናኛ ዘዴዎች የቀጥታ ስርጭት እገዳ አስፍኖአል። የአዉሮጻ ህብረትን ወክሎ በኬንያ የተከናወነዉን የምርጫ የተከታተለዉ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫዉ መስተጓጎሉን እና የተነገረዉ ዉጤት አጠራጣሪ መሆኑን ገልጾአል። በሌላ በኩል ኦዲንጋ የሚመሩት የብርቱካኑን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ነገ በናይሮቢ የሃዘን መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥሪ አቅርቦአል። መንግስት ተቃዋሚዉ ፓርቲ የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆኑን ይከሳል። በናይሮቢ ነገ ይደረጋል የተባለዉ የሃዘን መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ሌላ ደም እንዳያቃባ እያሰጋ ነዉ ዝርዝሩን ያድምጡ