ያሻቀበዉ የትራንስፖርት አደጋ በኢትዮጲያ | ዜና | DW | 22.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዜና

ያሻቀበዉ የትራንስፖርት አደጋ በኢትዮጲያ

በኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የሚመራ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ምክር ቤት መቋቋሙን በትራንስፖርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አቶ አሳልፈዉ አመዲን ለዶይቼ ቬሌ ገለፁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:21 ደቂቃ

የትራንስፖርት አደጋ በኢትዮጲያ

በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች እየጨመረ የመጣዉን አሰቃቂ የትራንስፖርት አደጋ ለመቅረፍ «መንገድ ትራፊክ ደንነት ምክር ቤት» በሚል ከኢትዮጵያ የመንገድና ትራንስፖርት ጉዳይ መሥርያ ቤት የተዉጣጡ ሚንስትሮች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም ዋና ዳይሬክተሮች የሚገኙበት ምክር ቤት ባሳለፍነዉ ቅዳሜ መቋቋሙን በትራንስፖርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቴር አቶ አሳልፈዉ አመዲን ለዶይቼ ቬሌ ተናግሯል። የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የትራንስፖርት ሚንስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ መሆናቸዉም ተገልፆአል።

በኢትዮጵያ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ በሚገኘዉ የመንገድ ትራንስፖርት አደጋ ምክንያት፤ ከመንጃ ፊቃድ አሰጣጥ እስከ የመንገድ ሕግጋትን አለማክበር ድረስና የሙስና መንሰራፋት መሆኑም ተመልክቶአል። በመንግስት በኩልም የወጣዉን የመንገድ ትራንስፖርት ሕግ የማስፈፀም ችለትኝነት እንደሚታይበት ነዉ የተመለከተዉ።

የአሽከርካር ብቃት ማረጋገጫ አሰጣትን አስመልክቶ በመንግስት በኩል የአሰራር መመርያ ወጥቶ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ አቶ አሳልፈዉ አመዲን ተናግረዋል። እንደ አቶ አሳልፈዉ አመዲን ገለፃ ሚኒስቴር መሥርያ ቤታቸዉ የአሽከርካር ማሰልጠኛ ተቋማትን እየፈተሸ እንደሆነና ሌሎች ለዚህ ችግር መንሴ ናቸዉ የተባሉትን እያየ መሆኑን ተናግረዋል። አሽከርካርዎች የመንገድ ትራንስፖርት ሕግጋትና ደንቦችን እንደማያከብሩ የብዙዎች አስተያየታት መሆኑ ይታወቃል። ለምሳሌ ይላሉ አቶ አሳልፈዉ አሽከርካርዎች የደሕነት ቀበቶ ማሰር አለባቸዉ የሚለዉ መመርያ ቢወጣም ተግባራዊ አለመሆኑን ይናገራሉ።
የተሽከርካሪና የአሽከርካር ጉዳይን አስመልክቶ ያለዉን ደንብና ሕግጋት ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በተፈለገዉ መጠን ባይሆንም ነገሩን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። አዲስ የመጡም የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርትን በተመለከተም የሚኒስትር መሥራያ ቤቱ ሚዲያዉን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ባለፈዉ ሳምንት የአዲስ አበባዉ ቀላል ባቡር ለመጀመርያ ጊዜም ግጭት ተከስቶ የአንድ ሰዉ ህይወት ማጥፋቱ ይታወቃል።
ሀገሪቱ ዉስጥ ያሉትን የመንገድ ትራንስፖርት ችግርን በተመለከተ በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ደረ-ገፅ ላይ በተደረገዉ ዉይይት ተሳታፊዎች አሳባቸዉን አጋርተዋል። ለምሳሌ እንደ አብዛኞች የመንገድ ትራፊኮች ትርፍ ሰው የጫነ ተሽከርካሪን እንጂ ከፍጥነት ወሰን በላይ የሚያሽከረክሩ ሹፊሮች ላይ ጭራሽ ቁጥጥር እንደማያደርጉ በአስተያየታቸዉ ገልጸዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic