ያልተቋጨዉ የደቡብ ሱዳን ድርድር | አፍሪቃ | DW | 19.11.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ያልተቋጨዉ የደቡብ ሱዳን ድርድር

በፍልሚያ ላይ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን የሁለቱም ተቀናቃኝ ኃይሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የሰላም አደራዳሪዎቹ አዲስ አበባ ላይ የጀመሩትን ዉይይት ቀጥለዋል።

ዉይይቱ አዲስ አበባ ዉስጥ ቀደም ሲል የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት አባል ሃገራት መሪዎች በተስማሙበት መሠረት የተካሄደ ሲሆን በሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የተደረሱ ስምምነቶችን ተግባራ የሚያደርግ መርሃግብር ለመንደፍ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች መካከል የሚካሄደዉ ዉጊያ እንዲያከትም የተጀመረዉ ጥረት እልባታ ያጣ መስሏል። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የአደራዳሪዉ ወገን ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ስዩም መስፍንን ስለድርድሩ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic