ያልተረጋጋችው ሶማልያ | አፍሪቃ | DW | 10.04.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ያልተረጋጋችው ሶማልያ

ባይዶዋ ሶማሊያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የገበያ ስፍራ ውስጥ የፈነዳ ቦምብ ቢያንስ 12 ሰዎችን እንደገደለ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የዓይን ምስክሮች ትናንት አስታውቀዋል። ሶማሊያን እንዴት ነው ማረጋጋት የሚቻለው? በርካታ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይላት በዘመቱባት ሀገር ለምን እስካሁን ሰላም ሊሰፍን አልቻለም?

ባይዶዋ ሶማሊያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የገበያ ስፍራ ውስጥ የፈነዳ ቦምብ ቢያንስ  12 ሰዎችን እንደገደለ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የዓይን ምስክሮች  ትናንት አስታውቀዋል። ሶማሊያን እንዴት ነው ማረጋጋት የሚቻለው? በርካታ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይላት በዘመቱባት ሀገር ለምን እስካሁን ሰላም ሊሰፍን አልቻለም?

ባይዶዋ በሶማሊያ በትልቀት በሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ከተማ ናት። ትናንት በከተማይቷ  በሚገኝ አንድ የአታክልት ገበያ  በፈነዳ ቦምብ ቢያንስ  12 ሰዎች ሲሞቱ  30 የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸው ተዘግቧል ። እንደ ጀርመን ዜና አገልግሎት ገለፃ የመንግሥት ወታደሮችን ለጫነ መኪና የታለመው ቦምብ ዒላማውን ስቶ በገበያተኞች ላይ ጥቃቱ ደርሷል።  የአሸባብ  ሚሊሺያዎች ጥቃቱን ያደረሰው ቡድናቸው መሆኑን ገልፀዋል።  የአገሪቷም ፖሊስ  አንድ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሏል።  «ንፁሀንን እና ደሀውን ህዝብ ገደሉት» ስትል ፋዱሞ ሃጂ የተባለች የአታክልት ነጋዴ የተመለከተችውን ለፖሊስ ገልፃለች። ከትናንቱ የቦንቡ ፍንዳታ በኋላ በማህበረሰቡ ዘንድ ስለሚታየው የደህንነት ሁኔታ። በሞቃዲሾ የሚገኘውን የዶይቸ ቬለ ዘጋቢ፤ ሁሴን አዌይስን

« አዎ! በርካታ መጨናነቅ እና ችግሮች አሉ። ግን ለማንኛውም ሶማሊያዊ የተለመደ ነው።  ምንም እንኳን ያለው ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እና አስቸጋሪ ቢሆንም ሰዉ እዛ መኖርን እየተወጣው ነው።»

 የሰቀቀን ኑሮ በሶማሊያ በየቦታው ይታያል።  እንደ ጀርመን ዜና አገልግሎት ገለፃ  በተለይ የባይዶዋ ከተማ  በየካቲት ወር የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ወታደሮች ከተማይቷን እስኪቆጣጠሩ ድረስ የእስላማዊው አማፂ ቡድን አሸባብ ዋና መቀመጫ ሆና ቆይታለች።

አማፂ ቡድኑ በድህረ ገፁ እንደፃፈው ከሆነ ቦምቡ የታለመው ለኢትዮጵያ ወታደሮች እና ለአጋሮቻቸው ነው።  በሚመጡት ወራት ተጨማሪ 2500 የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች በባይዶዋ ይሰፍራሉ ተብሎ ይጠበቃል።  ይሁንና በሶማሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች ይገኛሉ። እስካሁን መፍትሄ ሊገኝ ያልተቻለበትን ምክንያቶች የአለም አቀፍ የፀጥታ ምርምር ተቋም  በምህፃሩ ISS ቃል አቀባይ  ኤንድሩስ አሳሙአ ሲያብራሩ « ምክንያቱ ፤ ብዙውን ጊዜ የችግሩ ውስብስብነት በፍትሄ ፍለጋው ላይ አልተንፀባረቀም።  ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ሙከራዎች ቢደረጉም። ሙከራዎቹ በሙሉ በሶማሊያ ሰላም እንዲሰፍን ሊረዱ አልቻሉም።  ሶማሊያን እንደ አንድ አገር ብንመለከት ትልቅ ነች። ምንም እንኳን የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች እዛ ቢሰፍሩም በእያንዳንዱ ሜትር ወታደር ማሰማራት አይቻልም። ለዚህ ነው አክራሪዎቹ በቦንብ ጥቃት ስኬታማ ሊሆኑ የቻሉት።  ሁለተኛው ምክንያት እስላማዊ ቡድኑ የደፈጣ ውጊያ የማጥቃት ስልት የምንለውን የሚጠቀሙ መሆናቸው ነው።  ያም ማለት ንፁሀን መካከል ተደባልቀው ድርጊታቸውን መፈፀም ይችላሉ ማለት ነው።»

እነዚህ  እንደታቀደው የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪዎች ተልኮዋቸውን በድል ሊወጡ ያልቻሉበት ጥቂት ምክንያቶች ናቸው።  የሶማሊያ አማፂ ቡድን አሸባብ በሶማሊያ ሰላም እንዳይሰፍን ዋንኛ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። ስለሆነም የሚደረገው የኃይል ርምጃ መፍትሄ ካልሆነ፤ ሰላማዊ ድርድርን እንደ አማራጭ ማየት ይቻል ይሆን? ኤንድሩስ አሳሙአ « እኛም አማራጭ ይሆናል ብለን አስበን ነበር። ይሁንና በአሁኑ ሰዓት አዳጋች ነው።  እራሱ አሸባብ ከአልቃይዳ ጋ እንደተቀናጀ መግለፁ ራሱ፤ ድርድርን እንደ መፍትሄ ለማየት ከባድ ያደርገዋል።  እንደዛም ሆኖ ስለነሱ የበለጠ እንድናውቅ ይረዳን ነበር፤ ስለፍላጎታቸው፣ ስለሚያራምዱት እንቅስቃሴ፤ ካላቸው አክራሪ አቋም እንዲላቀቁ ይረዳ ነበር። እሱ መአቺው መፍትሄ ነው።  ግን  አሸባሪነትን የሚዋጋበት ሁኔታ ይህንን እንደአማራጭ ለማየት አዳጋች ያደርገዋል።»

የትናንቱን የቦንብ ጥቃት አስመልክቶ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዲዌሊ ሞሀመድ አሊ በአማፂ ቡድኑ የደረሰው አደጋ ባህላችንን እና የዕስልምና ዕምነትን የሚፃረር ነው ሲሉ አውግዘዋል። አሸባብን ሙሉ ለሙሉ ጨርሰን ከአገሪቱ እናስወጣለን ሲሉም ተስፋቸውን ገልፀዋል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 10.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14aXi

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 10.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14aXi