ያለ ውጤት ያበቃው የሱዳን ተወካዮች ድርድር | ኢትዮጵያ | DW | 13.10.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ያለ ውጤት ያበቃው የሱዳን ተወካዮች ድርድር

የሰሜን ሱዳን የደቡብ ሱዳን ተጠሪዎች የነዳጅ ዘይት ሀብት ክምችት ባላት በአቢዮ ግዛት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄዱት ድርድር ያለ ውጤት አበቅቷል ።

default

በአሜሪካን ሸምጋይነት ከአንድ ሳምንት በላይ በወሰደው በዚሁ ድርድር በግዛቲቱ በቅርቡ ህዝበ ውሳኔ ስለ ሚካሄድበት መንገድ ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻሉን ሁለቱ ወገኖች አስታውቀዋል ። ሆኖም የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ እንደዘገበው ተወካዮቹ ከሁለት ሳምንት በኋላ ድርድሩን ለመቀጠል ተስማምተዋል ።

ጌታቸው ተድላ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ