ያለ ውጤት የተቋረጠው የሱዳኖች ድርድር | አፍሪቃ | DW | 08.06.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ያለ ውጤት የተቋረጠው የሱዳኖች ድርድር

ሱዳንና ደቡብ ሱዳን አዲስ አበባ ውስጥ ሲያካሄዱ የቆዩት ንግግር ያለውጤት ተቋርጧል ። የካርቱምና የጁባ መንግሥታት ተደራዳሪዎች በሁለቱ ሃገራት ድንበር ላይ ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ የሆነ ቀጣና የት ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ መስማማት እንደተሰናቸው

ሱዳንና ደቡብ ሱዳን አዲስ አበባ ውስጥ ሲያካሄዱ የቆዩት ንግግር ያለውጤት ተቋርጧል ። የካርቱምና የጁባ መንግሥታት ተደራዳሪዎች በሁለቱ ሃገራት ድንበር ላይ ከጦር እንቅስቃሴ ነፃ የሆነ ቀጣና የት ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ መስማማት እንደተሰናቸው ባለሥልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል ። ያም ሆኖ በአፍሪቃ ህብረት ሸምጋይነት ለ10 ቀናት ሲካሄድ በቆየው በዚሁ ድርድር ሁለቱ ሃገራት በመርህ ደረጃ የጥላቻ ቅስቀሳና ግጭትን ለማቆም ወታደሮቻቸውንም ከአውዛጋቢ አካባቢዎች ለማስወጣትና አምፃያንንም መደገፍና ማሰጠጋትን ለማቆም መስማማታቸው ተዘግቧል ።የደቡብ ሱዳን ዋነኛ ተደራዳሪ ፓጋን አሙን ደቡብ ሱዳን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለመደራደርና ለችግሮቹም መፍትሄ ለመሻት ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃዋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 08.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15B4l
 • ቀን 08.06.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15B4l