ዩክሬይን እና የዩሊያ ቲሞሼንክ ዕጣ ፈንታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.04.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ዩክሬይን እና የዩሊያ ቲሞሼንክ ዕጣ ፈንታ

የቀድሞ የዩክሬይን ጠቅላይ ሚንስትር ዩሊያ ቲሞሼንኮ እአአ በ 2004 ዓም በዩክሬይን የተካሄደው ብርቱካናማ ዓብዮት በመባል የሚታወቀው የሕዝብ ዓመፅ ታዋቂ መሪ ነበሩ። አሁን ግን በሥልጣን ዘመናቸው ፈፅመዉታል በተባለዉ ሙስና ሰባት አመት እስራት ተፈርዶባቸው ባለፈው ነሀሴ ወር 2011ዓም ወህኒ የወረዱ ሲሆን፡

የእሥር ሁኔታቸውን በመቃወም ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ የረሀብ አድማ መተዋል። ይህና ካባድ የጤና እክል ያጋጠማቸው ቲሞሼንኮ ወደ ሐኪም ቤት ሲወሰዱ ሳለ በወህኒ ቤቱ ጠባቂዎቻቸው ተደብድበዋል በሚል የተሰማውም ዜና እንዳሳሰባቸው የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን እና ሩስያ ገልጸዋል።

በሰሜን ምሥራቅ ዩክሬይን በሚገኘው የቻሪኪቭ ወህኒ የረሀብ አድማ ከመቱ ዛሬ አምስተኛ ቀን የሆናቸው ቲሞሼንኮ እአአ በ 2005 እና ከ 2007 እስከ 2010 ዓም ድረስ ጠቅላይ ሚንስትር በነበሩበት ጊዜ ከሩስያ ጋዝ እንዲገዛ በተፈራረሙት ውል ሰበብ ነው ለእሥር የበቁት። በዛሬው ዕለት በአንጻራቸው አዲስ ችሎት የሚከፈትባቸው ቲሞሼንኮ ባደረባቸው ከባድ የጀርባ ሕመም ምክንያት ባለፈው የሣምንት መጨረሻ ሐኪም ቤት በተወሰዱበት ጊዜ የመደብደብ ምልክት እንደታየባቸው ጠበቃቸው ሴርጌይ ቭላሴንኮ አረጋግጠዋል።
« ዩሊያ ቲሞሼንኮ ባለፈው ዓርብ በወህኒ ቤቱ ጠባቂዎች ተደብድበዋል። በሆዳቸዉና እጆቻቸዉ ላይ ደም የቋጠሩ ቁስሎች ታይተዋል። ቲሞሼንኮ ካለፈቃዳቸው በግድ ሰው ተሸክሞ መኪና ውስጥ አስገብቶ ወደ ሐኪም ቤት ወስዷቸዋል። ባለፈው እሁድ ደግሞ ወደ ወህኒ ቤት መልሰዋቸዋል። »


ቲሞሼንኮ በመታመማቸው ወደ ሐኪም ቤት መወሰዳቸውን ቢያረጋግጥም፡ ተደብድበዋል መባሉን ሀሰት ሲሉ አስተባብለዋል፤ ሐኪም ቤት ከደረሱ በኋላ ሕክምና እንዲደረግላቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸውም ወደ ወህኒ ቤት እንዲመለሱ መደረጉን ዓቃቤው ሕግ አክለው ገልጸዋል።
ካሁን ቀደም ከቤርሊን በሄዱ ጀርመናውያን ዶክተሮች ሕክምና ተደርጎላቸው የነበሩት ቲሞሼንኮ  ወደሌላ አውሮጳዊ ሀገር ሄደው እንዲታከሙ ለማስቻል ዩክሬይን ሕጉን ለማሻሻል ዝግጁ መሆንዋን የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ቫለሪ ኮሮሽኮቭስኪ ገልፀዋል። በምላሹ የአውሮጳ ህብረት ከዩክሬይን ጋ በእንጥልጥል ያለውን የፖለቲካ እና የንግድ ውልን እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል። ይሁንና፡ ህብረቱ የቲሞሼንኮ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ፡ አንዳንዶች አውሮጳውያን ባለሥልጣናት እንደሚሉትም፡ የቀድሞዋ ጠቅላይ ሚንስትር ሳይፈቱ ውሉን እንደማያጸድቅ አስታውቋል።
የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ በዩክሬይን ላይ ያለውን የምዕራቡን ዓለም ቅሬታ ለማሳየት ሲሉ በሚቀጥለው ግንቦት ወር በዩክሬይን ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰርዘዋል። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ የፍትሑ አውታር ለፖለቲካው ንትርክ መሣሪያ መሆን እንደማይገባው አሳስበዋል።
« ዩክሬይን ከአውሮጳ ህብረት ጋ በይበልጥ ለመቀራረብ ከፈለገች የሕግ የበላይነትን የመሳሰሉትን መሠረታዊ አውሮጳውያን እሴቶች ማክበር አንዱ ቅድመ ግዴታ ነው። በዚሁ ቅድመ ግዴታ ውስጥ የወንጀለኛ መቅጫው ሕግ ለፖለቲካው ውዝግብ መሣሪያ መሆን የለበትም የሚለው ሀሳብ ይገኝበታል። »
የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫም፡ የዩሊያ ቲሞሼንኮ መብት እንዲከበር ከመጠየቁ ጎን፡ የሀገሪቱን ውስጣዊ ችግሮች ሳያባብሱ ለተፈጠረው ውዝግብ መፍትሔ እንዲፈለግለት ጠይቆዋል።

Ukrainian opposition leader and presidential candidate Viktor Yanukovych speaks to the media in Kiev, Ukraine, Sunday, Feb. 7, 2010. Exit polls showed pro-Russian opposition leader Viktor Yanukovych with a narrow lead Sunday in Ukraine's presidential runoff _ a result that could restore much of Moscow's influence in a country that has labored to build bridges to the West. (AP Photo/Sergei Chuzavkov)

ፕሬዚደንት ያኑኮቪች


ዩክሬይን እና ፖላንድ እአአ ከሰኔ ስምንት እስከ ሀምሌ አንድ ቀን ድረስ የአውሮጳ እግር ኳስ ዋንጫ ግጥሚያን ሊያስተናግዱ ስድስት ሣምንታት በቀረው ባሁኑ ጊዜ በምዕራቡና በዩክሬይን መካከል በቲሞሼንኮ ሰበብ ውዝግቡ እየተጠናከረ መጥቶዋል። ባለፈው ሣምንት በማጭበርበርና ግብር ባለመክፈል ሌላ አዲስ ክስ የተመሠረተባቸው ቲሞሼንኮ እና ምዕራቡ ዓለም ክሱን ፕሬዚደንት ያኑኮቪች ተቀናቃኛቸውን ለመጉዳት እንዳደረጉት ነው የተመለከቱት።
 ጠበቃቸው ሴርጌይ ቭላሴንኮ የችሎቱን ሂደት ተዓማኒነት የሌለው ሲሉ ወቅሰዋል።
« ለዩሊያ ቲሞሼንኮ የሚሟገተው ቡድን፡ ልክ እንደ ዘጠና ዘጠኝ ከመቶው የሀገሪቱ ሕዝብ በዩክሬይን የፍትሕ አውታር ላይ እምነት የለውም። በዚህም የተነሳ ከዩክሬይን ውጭ ያሉ ፍርድ ቤቶችን ከለላ እናፈላልጋለን። »
ጠበቃው ቭላሴንኮ በዚሁ አነጋገራቸው የቲሞሼንኮን ጉዳይ የቀድሞዋ የዩክሬይን ጠቅላይ ሚንስትር ተገቢው ሕክምና እንዲደረግላቸው ባለፈው ወር ጥያቄ ላሳሰበው የአውሮጳ የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት ለማቅረብ ዕቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል። በዩክሬይን ትልቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን በቲሞሼንኮ ላይ ተፈፀመ የተባለው በደል እንዲጣራ ጠይቋል።

ማርኩስ ዛምባሌ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 26.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14lOm
 • ቀን 26.04.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14lOm