ዩኤስ አሜሪካ በፅንፈኞች ላይ ያላት አቋም | አፍሪቃ | DW | 13.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ዩኤስ አሜሪካ በፅንፈኞች ላይ ያላት አቋም

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ጀሀዲስቶችን ለማጥቃት ያወጡት እቅድ እና በሶማልያ ጽንፈኞች የተገደሉት አንድ የደህንነት ባለስልጣን

የዩኤስ አሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ሀገራቸዉ እራሱን «እስላማዊ መንግሥት» ብሎ የሚጠራዉን አማፂ ቡድን ለመዋጋት ደጋፊ ሀገራትን ለማሰባሰብ የጀመሩትን ሥራ ቀጥለዋል። ኬሪ ዛሬ ካይሮ ላይ ከፕሬዚዳን አብደል ፈታህ አልሲሲ እና ከአረብ ሊጉ ዋና ፀሐፊ ናቢል አል-አላረቢ ጋር ተነጋግረዋል። እንደ አንድ የዩኤስ አሜሪካ ባለሥልጣን እምነት፤ ዩኤስ አሜሪካ ጀሀዲስቶቹን ለማጥቃት በሚደረገዉ ጥረት፤ የግብፅ የሐይማኖት ተቋማት ድርጊቱን እንዲደግፉ ትፈልጋለች። ባለፈዉ ረቡዕ ባራክ ኦባማ «እስላማዊ መንግሥት » የተሰኘዉን አማፂ ቡድን ለመደምሰ እቅድ ካወጡ በኋላ ግብፅና ሌሎች ዘጠኝ የአረብ ሀገራት ጀሀዲስቶችን ለመዋጋት ድጋፍ ለመስጠት መስማማታቸዉ ይታወቃል።

Somalia Mogadischu Al-Shabaab Kämpfer ARCHIV

ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለዉ የሚነገርለት የአሸባብ ቡድን

ዮናይትድ ስቴትስ ኢራቅ ውስጥ እራሱን «እስላማዊ መንግሥት» ብሎ የሚጠራዉን አማፂ ቡድን ላይ ብቻ አይደለም ውጊያ የጀመረችው። ሶማሊያ በሚገኘው የአሸባብ አማፂ ቡድን ላይም ከሁለት ሳምንት በፊት በሰው አልባ አይሮፕላን ጥቃት መጣሏ ይታወሳል። በዚህም የሶማልያዉ የአሸባብ ቡድን መሪ ከተገደለ በኋላ ዛሬ አንድ የሶማልያ ብሄራዊ ደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን መቃዲሾ መኪና በማሽከርከር ላይ ሳሉ በጥይት ተመተው መገደላቸዉን ሮይተርስ ዘገበ። አንድ ማንነታቸዉን መግለፅ ያልፈለጉ የሶማልያ የደህንነት ቢሮ ባለስልጣን እንደገለፁት፤ ዛሬ የተገደሉት ባለስልጣን በቅርቡ የሀገሪቱ ፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ባለሥልጣን ምክትል ተጠሪ ሆነዉ የተሾሙት ሞሃመድ ካኑኒ ናቸዉ። መቃዲሾ ዉስጥ አንድ ታጣቂ የሚሽከረክሩትን መኪና አስቁሞ ነዉ ጥይት ያርከፈከፈባቸዉ። ዛሬ የተገደሉት ባለስልጣን ከሁለት ወር በፊት የተገደሉትን፤ ባለስልጣን ቦታ የተኩ እንደነበርም የሶማልያ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። የዮናይትድ ስቴትስ የሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አሸባብ ላይ የምታራምደው ፖሊሲ የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ ርዕሰ ጉዳያችን ነው።

አበበ ፈለቀ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic