ዩኤስ አሜሪካ ሰሜን ኮርያ ዉዝግብ | ዓለም | DW | 14.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ዩኤስ አሜሪካ ሰሜን ኮርያ ዉዝግብ

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኮርያ መንግሥት ላይ የምታደርሰዉ ጫና በርትቷል። ቻይና በበኩልዋ በኮርያዉ ግጭት ዩናይትድ ስቱትስና የፕዮንግያንግ መንግሥት ኃይላቸዉን ለማሳየት ከሚያደርጉት ፍጥጫ እንዲታቀቡ አሳሰበች።  እንደ ምሁራን ግምት ሰሜን ኮርያ የአቶም ጦር መሳርያ ሙከራ በቅርቡ ታደርጋለች።

ዩዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኮርያ መንግሥት ላይ የምታደርሰዉ ጫና በርትቷል። ሰሜን ኮርያ በቀጣይ የሮኬት ሙከራ ማካሄድ የምትፈልግ ከሆነ የአሜሪካን የፀጥታ ኃይላት ቅድመ መከላከያ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸዉን «NBC» የተሰኘዉ የዩናይትድ ስቴትስ ቴሌቭዝን አንድ የአሜሪካን የደሕንነት ባልደረባን ጠቅሶ ዘግቦአል። በኮርያ ልሳነ ምድር አካባቢ በራሪ ሮኬቶችንን የጫኑ ሁለት የአሜሪካን መርከቦች በተጠንቀቅ እንደሚገኙም ተዘግቦአል። ይህን መረጃ በተመለከተ ግን የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቦአል። ቻይና እና ሩስያ በበኩላቸዉ ሰሜን ኮርያ ምንም አይነት ጠብ አቻሪነትን እንዳታሳይ የፒዮንግያንግ መንግስትን አስጠንቅቀዋል። የሰሜን ኮርያ ምክትል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃን ሶንግ ራዮል ሰሜን ኮርያ ሳትሆን ዩናይትድ ስቴትስ ናት ጠብ አጫሪዋ ሲሉ ተናግረዋል።  

« ሰሜን ኮርያ ሳትሆን ዩናይትድ ስቴትስ ማለት ዶናልድ ትራምፕ ናቸዉ ችግር እየፈጠሩ ያሉት። ይህን ያልኩበት ምክንያት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸዉ ሰሜን ኮርያ ችግር ታነሳለች ስላሉ ነዉ። ከዩናይትድ ስቱትስ ሌላ ወደ ሰሜን ኮርያ ግዙፍ የሆነ ወታደራዊ ልምምድን ከደቡብ ኮርያ ጋር እንዲሁም ፤አዉስትራልያ ላይ ገደብ የነበረዉ  የኒኩልየር ጦር አዉሮፕላን ተሸካሚ  ወደ ኮርያ ልሳነ ምድር እየመጣ ነዉ።  »
ቻይና በበኩልዋ በኮርያዉ ግጭት ዩናይትድ ስቱትስና የፕዮንግያንግ መንግሥት ኃይላቸዉን ለማሳየት ከሚያደርጉት ፍጥጫ እንዲታቀቡ አሳሰበች።  እንደ ምሁራን ግምት ሰሜን ኮርያ የአቶም ጦር መሳርያ ሙከራ በቅርቡ ታደርጋለች። ሰሜን ኮርያ ነገ ቅዳሜ የሀገሪቱ መንግሥት መሥራች የኪም ሱንግ ሁለተኛ 105 ኛ ዓመት ልደት በዓል በልዩ ልዩ ወታደራዊ ስነስርዓቶች ታከብራለች ተብሎ ይጠበቃል ። ባለፉት ቀናት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮርያ የጀመረችዉን ማንኛዉንም የአቶም መርሃ ግብር አጋርዋ ቻይና እንድታስቆም ካላደረገች ዩናይትድ ስቴትስ በራስዋ ታስቆማታለች ሱሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።       
 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ