ዩኤስ ለአፍሪቃ የሾመቻቸው አዲሱ ረዳት ሚኒስትር | አፍሪቃ | DW | 04.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ዩኤስ ለአፍሪቃ የሾመቻቸው አዲሱ ረዳት ሚኒስትር

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ዶናልድ ያማማቶ የአፍሪቃ ረዳት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። አምባሳደር ያማማቶ አዲስ ለተሾሙለት ቢሮ ነገ ሥራ ይጀምራሉ። ያማማቶ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለሶስት አመታት በአምባሳደርነት አገልግለዋል። በጁቡቲም አምባሳደር ሆነው ያውቃሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:38
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:38 ደቂቃ

የዶናልድ ያማማቶ ሹመት

የአሜሪካ መንግሥት የዲፕሎማሲ ማዕከል ድረ-ገፅ እንደሚጠቁመው አምባሳደሩ ከጎርጎሮሳዊው 2003 እስከ 2006 ዓ.ም. በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር የአፍሪቃ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነው አገልግለዋል። አፍሪቃን ችላ ብሏል እየተባለ የሚወቀሰው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቦታው ሌሎች ሁለት እጩዎች ለመሾም ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቶ ነበር።


መክብብ ሸዋ 
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ
 

Audios and videos on the topic