ዩናይትድ ስቴትስ ተደጋጋሚ ፍንዳታ | ዓለም | DW | 18.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ዩናይትድ ስቴትስ ተደጋጋሚ ፍንዳታ

ለሐገሪቱ ፕሬዝዳት፥ ለአንድ የምክር ቤት እንደራሴና ለአንዲት ዳኛ ገዳይ መርዝ የታሸገበት ደብዳቤ ተልኮ በፀጥታ አስከባሪዎች ተይዟል።የቦስተኑን ቦምቦች አፍንድተዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ሰዎች መገኘታቸዉ ሲነገር፥ የሰዎቹ ማንነትና አላማ እስካሁን በይፋ አልተነገረም።

አሜሪካዉያን ቦስተን ዉስጥ የማራቶን ሩጫ ዉድድር እንደተጠናቀቀ በመሮጪያዉ መንገድ አጠገብ የፈነዱ ሁለት ቦምቦች የገደሏቸዉን ሰወስት ሰዎች ዛሬ-ለመዘከር ሲዘጋጁ ዌስት-ቴክስሳ ዉስጥ አንድ የማዳበሪያ ፋብሪካ ፈንድቶ ሃያ ሐይል ሰዎች ገድሏል።በመቶ የሚቆጠሩ አቁስሏል።አደጋዉ የደረሰበት ምክንያት በዉል አልታወቀም።በመሐሉ ለሐገሪቱ ፕሬዝዳት፥ ለአንድ የምክር ቤት እንደራሴና ለአንዲት ዳኛ ገዳይ መርዝ የታሸገበት ደብዳቤ ተልኮ በፀጥታ አስከባሪዎች ተይዟል።የቦስተኑን ቦምቦች አፍንድተዋል ተብለዉ የተጠጠረጠሩ ሰዎች መገኘታቸዉ ሲነገር፥ የሰዎቹ ማንነትና አላማ እስካሁን በይፋ አልተነገረም። ተደጋጋሚዉ አደጋና የአደጋ ሙከራዉን በተመለከተ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ 

Audios and videos on the topic