ዩኒሴፍ፤ በምግብ እጦት የህጻናት ሞት ጨምሮአል | ዓለም | DW | 17.05.2022
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ዩኒሴፍ፤ በምግብ እጦት የህጻናት ሞት ጨምሮአል

በዓለማችን በምግብ እጦት በዓመት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህጻናት እንደሚሞቱ ተነገረ። የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት «ዩኒሴፍ» ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መረጃ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፤ ወደ 45 ሚሊዮን ህጻናት በረሃብ እየተሰቃዩ ነዉ።

በዓለማችን በምግብ እጦት በዓመት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህጻናት እንደሚሞቱ ተነገረ። የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት «ዩኒሴፍ» ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መረጃ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፤ ወደ 45 ሚሊዮን ህጻናት በረሃብ እየተሰቃዩ ነዉ። የኮሮና ወረርሽኝ፣ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዙ በሚከሰቱ ቀውሶች እና በተለያዩ ቦታዎች በሚታዩ የትጥቅ ትግልና የድህነት ስጋት ምክንያት የምግብ ዋስትና እጦትን በማስከተሉ፤ የተጎጂ ህጻናት ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን የዓለሙ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አስታዉቋል። በጦርነት ዉስጥ ካለችዉ ከዩክሬን ወደ ተለያዩ ሃገራት ይገባ የነበረዉ የስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የእህል አቅርቦት እጥረት ሁኔታውን እንዳባባሰዉም ተመልክቶአል።  

 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ