የVOA መታወክና ውዝግቡ | ኢትዮጵያ | DW | 10.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የVOA መታወክና ውዝግቡ

የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ በተለይም የአማርኛ ስርጭት ከሁለት ሳምንት ወዲህ በኢትዮጵያ እንዳይሰማ በሞገድ ታውኳል የሚለው ወቀሳ አሁንም እንደቀጠለ ነው ።

default

የጣቢያው ባለሥልጣናት እንደሚሉት ስርጭቱ መታወኩን እንጂ አዋኪውን ለይተው አላወቁትም ። ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ድርጅት CPJ እና አንድ የመገናኛ ዘዴዎች ምሁር ግን ለዶይቼቬለ በሰጡት አስተያየት ድርጊቱ ሊፈፀም የሚችለው በመንግስት ብቻ ነው ብለዋል ።የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የአማርኛ ስርጭት በኢትዮጵያ እንዳይሰማ በሞገድ የማወክ ድርጊት ሊፈፀም የሚችለው በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ነው የሚለውን ወቀሳ መንግስት መሠረተ ቢስ ወቀሳ በማለት አስተባበሎታል ። የኢትዮጵያ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ዴታ አቶ ሽመልስ ከማል ዛሬ ለዶይቼቬለ እንዳስታወቁት የታገደ ስርጭት የለም ። መንግስታቸውም አለአግባብ ዘገባዎች ያሰራጫሉ የሚላቸውን በፍርድ ቤት ከመክሰሰ በስተቀር እንዲህ ዓይነት ዕርምጃ ወስዶ አያውቅም ብለዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲዝርዝሩን ልኮልናል ። አቶ ሽመልስን ልደት አበበ አነጋግራቸዋለች ።

ሒሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ