የIMF ዳይሬክተር መያዝ | ዓለም | DW | 16.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የIMF ዳይሬክተር መያዝ

ሰሞኑን መነጋገሪያ ከሆኑ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አንዱ የአለም ገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ፕሬዝዳንት የዶሚኒክ ሽትራውስ ካን በመሲብ መድፈር የመጠርጠርና በኒውዮርክ ፖሊስ የመያዝ ጉዳይ ነው።

default

ዶሚኒክ ሽትራውስ ካን

ሽትራውስ የሆቴል ሰራተኛ የሆነችን ሴት ለመድፈር ሙከራ በማድረግ ተጠርጥረው ትላንት በፖሊስ ተይዘዋል። የሽትራውስ በዚህ ጉዳይ መጠርጠር ብዙዎችን አነጋግሯል። በተለይም የፈረንሳይ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚወዳደሩና የቅድመ ግምት አስተያየቶችም ወደእሳቸው ባጋደለበት ወቅት ላይ ይህ መሰማቱ ከማነጋገር ባለፈ አስገራሚ አድርጎታል። ዛሬ የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ሚኒስትሮች በብራስልስ ተገናኝተው በሚወያዩበት ወሳን ስብሰባ ላይ እሽትራውስ ይጠበቁ ነበር። ወደ ብራስልስ ስልክ በመደወል እዚያ ያለውን ዘጋቢያችንን ገበያው ነጉሴን አነጋግሬው ነበር።

ገበያው ንጉሴ

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ