የICC እና አፍሪቃ ግንኙነት | ዓለም | DW | 08.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

    የICC እና አፍሪቃ ግንኙነት

የአፍሪቃዉያንን ያክል አባላት የሌሉት ፍርድ ቤት እስካሁን ከአፍሪቃዉያን ዉጪ የከሰሰ፤ ያሳሰረ ወይም ያስፈረደበት የለም።ይሕ በርካታ የአፍሪቃ መንግሥታትን ቅር አስኝቷል።እንደ ደቡብ አፍሪቃ፤ ቡሩንዲ እና ጋምቢያን የመሳሰሉ ሐገራት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎች እንሱን ለመከተል እያንገራገሩ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:33
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:33 ደቂቃ

ICC እና አፍሪቃ

የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) የመልዕክተኞች የፍርድ ቤቱ አባል ከሆኑ ከ13ት የአፍሪቃ መንግሥታት እና ከአፍሪቃ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር አዲስ አበባ ዉስጥ ተወያተዋል። ፍርድ ቤቱ እንዳስታወቀዉ ዉይይቱ ሥለፍርድ ቤቱ አሠራር እና ከአባል ሐገራት በሚጠበቀዉ ትብብር ላይ ያተኮረ ነዉ።የአፍሪቃ መንግስታት በፍርድ ቤቱ  ሥራ እና አሰራር ላይ ቅሬታቸዉን በሚገልጡበት ባሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዉስጥ የተደረገዉ ዉይይት በሁለቱ ወገኖች መካከል በተከታታይ የሚደረጉት ዉይይቶችና ምክክሮች  አካል ነዉ።

 

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) የአፍሪቃዉያንን ያክል በርካታ አባላት ከሌላ ክፍለ ዓለም የለዉም።ሰላሳ-አራት።ፍርድ ቤቱ፤ ይሕን ያኽል አባላት ካሉት አሁጉር ተወካዮች ጋር ሥለሥራ፤ አሰራሩና ሥለሚጠብቀዉ ትብብር መነጋገር አስፈላጊ፤ ጠቃሚ፤ የፍርድ

Internationaler Strafgerichtshof mit Logo

ቤቱ ደንብም ነዉ -ይላሉ የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ፋዲ ኤል አብደላሕ።«ከICC ደንቦች አንዱ ሁለቱንም ወገኖች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከነዚሕ አባል መንግስታት ጋር መነጋገር እና ሥለ አሰራሩ ማስረዳት ነዉ።ሥለ ትብብር፤ ሥለ ፍርድ ቤቱ ሥልጣን፤ የመደጋገፍ መርሆዎችን አስፈላጊነት--እነዚሕ ሁሉ ትናንትና ከትናንት ወዲያ በተደረጉት ዉይይቶች ተነስተዋል።»

 

ዋናዉ ግን የአፍሪቃዉያን እና የፍርድ ቤቱ አለመግባባት ነዉ።የአፍሪቃዉያንን ያክል አባላት የሌሉት ፍርድ ቤት እስካሁን ከአፍሪቃዉያን ዉጪ የከሰሰ፤ ያሳሰረ ወይም ያስፈረደበት የለም።ይሕ በርካታ የአፍሪቃ መንግሥታትን ቅር አስኝቷል።እንደ ደቡብ አፍሪቃ፤ ቡሩንዲ እና ጋምቢያን የመሳሰሉ ሐገራት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎች እንሱን ለመከተል እያንገራገሩ ነዉ።

በ1990ዎቹ ማብቂያ የሩዋንዳን የዘር ጭፍጨፋ የዳኘዉ የተባበሩት መንግሥታት ፍርድ ቤት ከፍተኛ አቃቤ ሕግ የነበሩት ዶክተር ያቆብ ኃይለማርያም የአፍሪቃዉያንን ወቀሳ አስገራሚ፤ አስቂኝም ይሉታል።

                      

ፍርድ ቤቱ አፍሪቃዉያን ብቻ ይከሳል፤ ያሳስራል ይወነጅላል የሚለዉንም ወቀሳ ዶክተር ያቆብ፤ «ታዲያ ማን ይከሰስ» -ዓይነት ይላሉ።

                                

የፍርድ

g.jpg (DPA)

ቤቱ ቃል አቀባይ ፋዲ ኤል አብደላሕ እንደሚሉት የቅሬታ፤ ልዩነቱ ሰበብ-ምክንያት ምንም ሆነ ምን አብነቱ ዉይይቱን መቀጠል ነዉ።የአዲስ አበባዉም ስብሰባ የተከታታዩ ዉይይት አካል ነዉ።«እንደሚመስለኝ ገንቢ ዉይይቱን መቀጠል፤አጠራጣሪ ሐሳቦችን ማጥራት፤ የአባል መንግስታትን ሥጋት ማዉጣት እና በተገቢዉ መድረክ መፍትሔ መፈለግ፤ ፍርድ ቤቱ ከአባላቱ በተሰጠዉ ሥልጣን መሠረት ሥለሚያከናዉናቸዉ ምግባራት ማስረዳት ጠቃሚ ነዉ።»ቃል አቀባዩ ዉይይቱ ጥሩ ዉጤት ያመጣል የሚል ተስፋ አላቸዉ።ዶክተር ያቆብ ግን «ሲሆን ለማየት ያብቃን።»

                           

እስካሁን ዉይይት መደረጉ እንጂ ዉጤቱ በርግጥ አልታወቀም።

 

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

 

  

 

Audios and videos on the topic