የHIV ምርመራ ሳምንት በድሬዳዋ | ኢትዮጵያ | DW | 03.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የHIV ምርመራ ሳምንት በድሬዳዋ

በድሬዳዋ መስተዳድር በዚህ ሳምንት ስለ HIV ስርጭትና የመከላከያ መንገዶች የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በፈቃደኘት ላይ የተመሰረተ ምርመራም እየተካሄደ ነው ።

default

..ይመርመሩ ራስዎን ይወቁ ....

በዚሁ ሳምንትም በርካታ ነዋሪዎች በደማቸው ውስጥ HIV መኖር አለመኖሩን ለማወቅ አገልግሎቱን ለመስጠት ወደ ተዘጋጁት ቦታዎች በመምጣት በፈቃደኝነት ይመረመራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመስተዳድሩ በተለይ በገጠሩ አካባቢ በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል ይረዳል ብሎ ባመነው መሰረት ጋብቻዎች ከመፈፀማቸው በፊት የHIV ምርመራ መካሄዱ እንደ አንድ ቅድመ ግዴታ ተደንግጓል ። በሌላም በኩል በኢትዮጵያ ጅቡቲና ሶማሌላንድ መካከል የድንበር ተሻጋሪ የ HIV ክትትል ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ከድሬዳዋ ዘግቧል ።