የFAO የምግብ እጥረት ዘገባ | ዓለም | DW | 16.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የFAO የምግብ እጥረት ዘገባ

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት FAO ካለፉት 15ዓመታት ወዲህ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸዉ ወገኖች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ925ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን አስታወቀ።

default

እንዲያም ሆኖ በዓለም የተፈጠረዉን የፋይናንስና የኤኮኖሚ ቀዉስ ተከትሎ በቂ ምግብ የሚያስፈልገዉ ህዝብ ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን እንደሚልቅ ጠቁሟል። የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አሁን ክፉና የሚያጠቃዉ ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ አገራትን ሲሆን። ሁለት ሶትተኛዉ ቁጥር በሰባት አገራት ይገኛል። እነሱም ባንግላዴሽ፤ ቻይና፤ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፤ ኢትዮጵያ፤ ህንድ፤ ኢንዶኔዢያና ፓኪስታን መሆናቸዉን የFAO ዘገባ ያስረዳል። ድርጅቱ በዘገባዉ እንዳመለከተዉ በየስድስት ሰከንዱ አንድ ህፃን ከርሃብ ጋ በተገናኘ በሽታ ምክንያት ይቀጠፋል።

ተኽለእግዚ ገ/እየሱስ፤ ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ