የFAO አዲስ ዳይሬክተር | ዓለም | DW | 27.06.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የFAO አዲስ ዳይሬክተር

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት FAO ላለፉት 17ዓመታት የመሩትን የድርጅቱን ዋና ጸሐፊ በአዲስ ተካ።

default

ዋና ጽህፈት ቤቱ በሚገኝባት ሮም ከተማ 37ኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን በማካሄድ ላይ ያለዉ FAOን ከመጪዉ የአዉሮጳዉያን ዓመት መባቻ አንስተዉ የሚመሩት ብራዚሊያዊዉ ጁዜ ግራዚያኖ ዳ ሲልቫ ይሆናሉ። ከስድስት እጮዎች ጋ ተፎካክረዉ በድምፅ ብልጫ ያሸነፉት ግራዚያኖ ዳ ሲልቫ የብራዚል የምግብ ዋስትና ሚኒስትር ሆነዉ አገልግለዋል። ለዓመታት FAOን በኃላፊነት የመሩት ጃክስ ዲዩፍ በተለይ የፋይናንስ ቀዉስ ከተከሰተበት ከአዉሮጳዉያኑ 2008ዓ,ም ወዲህ የምግብ ዋጋ መናር ለድርጅቱ ዋነኛ ተግዳሮት እንደሆነ ሲያሳስቡ ከርመዋል። እሳቸዉን የሚተኳቸዉ አዲሱ ተመራጭ በአገራቸዉ ረሃብን ለማጥፋት የተጠቀሙበትን ብራዚልን ከረሃብ ነፃ ያደረገ ስልት ለዓለም አዉለዋለሁ እያሉ ነዉ። በዓለማችን ለረሃብ የተጋለጠዉ ሕዝብ አንድ መቶ ሚሊዮን መድረሱ እየተነገረ ነዉ።

ተኽለእግዚ ገ/እየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic