የACP ሃገሮች እና የአዉሮጳ ጉባኤ | አፍሪቃ | DW | 21.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የACP ሃገሮች እና የአዉሮጳ ጉባኤ

25ኛዉ የአፍሪቃ ፓስፊክና ካረቢያን በእንግሊዝኛዉ ምህጻር ACP ሃገሮች እና የአዉሮጳ ፓርላማ ጉባኤ የማዳጋስካርና ኤርትራ መንግስታት የዜጎቻቸዉን መብት እንዲያከብሩ አሳሰበ።

ለሶስት ቀናት ብራስል በአዉሮጳ ፓርላማ የተካሄደዉ የASP ሃገሮች እንደራሴዎችና የአዉሮጳ ፓርላማ አባላት የጋራ ጉባኤ በያዝነዉ ሳምንት ተጠናቋል። ጉባኤዉ የሚካሄደዉ ቀደም ሲል በተፈረመዉ የኮቶኑ ስምምነት መሠረት ሲሆን ዓላማዉ በአዉሮጳ ኅብረትና በACP ሃገሮች መካከል ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር፤ የልማት ትብብሮችን ለማሳደግ እና በተለይ በACP ሃገሮች የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ እንዲሻሻልና ዴሞክራሲያዊ አሰራሮች እንዲጎለብቱ ነዉ።

የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ልኮልናል

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic