የ2015 የልማት ፕሮግራምና የባለሞያ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 21.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የ2015 የልማት ፕሮግራምና የባለሞያ አስተያየት

የ2015 የልማት ፕሮግራም የሰዉ ልጅ ልማት አመልካች ዘገባ፤ በኢትዮጵያ የሚታየዉ ዉስብስብ ድሕነት 78,9 ሚልዮን ሕዝብ በቀን ከ 1,25 ዶላር በታች ገቢ ያላቸዉ፤ በትምህርት እጦት በጣም የተጎዱና በምግብ እጥረት የተነሳ ዝቅተኛ ተመጋቢ ኅብረተሰብ የሚገኝባትና ከፍተኛ የንፁሕ መጠጥ ዉኃ እጥረት የሚታይባት አገር እንደሆነች ያትታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:21 ደቂቃ

የልማት ፕሮግራምና የባለሞያ አስተያየት

በሰዉ ልጅ ልማት አመልካች ጥናት ዘገባዉ ከተካተቱት 188 አገሮች መካከል ኢትዮጵያ 174ኛ ደረጃ ላይ መሆንዋና ያልጠመጣጠነ ልማት እንዳላትም ተጠቅሶዋል። በፈርንጆች አቆጣጠር በ2014 ዓ,ም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ከሚገኙት አገራት ሌላ ብዙ አገሮች ከነበሩበት ከድሕነት ወለል በታች ወደ መካከለኛዉ የድሕነት መለክያ ወለል እንደገቡ ያትታል። «ለሰዉ ልማት ሥራ» በሚል ርፅስ ይዞ የወጣዉ ይህ ጥናት ባለፉት 25 ዓመታት ሁለት ብሊዮን ሰዎች ከታችኛዉ የሰዉ ልጅ ልማት ወለል መለክያ ዉስጥ እንደ ወጡ ያሳያል።


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በጥናቱ መክፈቻ ላይ በደረጉት ንግግር የኤኮኖሚዉ አንቀሻቃሽ ቋሚ ሥራ በመሆኑ፤ ማኅበረሰቡ ከቋሚ ስራ እድል መጠቀም አለበት ሲሉ ተናግረዋል። ከዓለማችን 850 ሚልዮን ሰዎች የሥራ ደሆች ሰሆኑ ገብያቸዉም ከ2 ዶላርስ በታች ነዉ። ከ200 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሥራ አጥ ሲሆን ከዚህ መካከል ደግሞ 74 ሚሊዮኑ ወጣቶች ናቸዉ ። 21 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በጉልበት ሥራ ዉስጥ እንደሚገኙ መሆናቸዉን ጥናቱ ያትታል።
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኤኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል የማይክሮ ኤኮኖሚክስና የእድገት ፖሊሲ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ይህ ጉዳይ አስመልክቶ ለዶቼ ቬሌ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግሥት ደህነትን የሚለካዉ በገቢ ላይ ተመሥርቶ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል። እንደ መንግሥት ስሌት ይላሉ ፕሮፊሰሩ ለምሳሌ አንድ ሰዉ በወር 300 ብር ማለት በቀን 10 ብር ገቢ ካለዉ ከዝያ ዉስጥ 5 ብሩን ለምግቡ ቢያወጣ የቀርዉን ደግሞ ለትራንስፖርቱ፣ ለቤት ክራይ፣ ለሳሙና፣ ለዘይትና ለሌላ ሌላ ነገር ከተጠቀመበት ግለሰቡ ደሃ አይደለም።


<<አሁን ባለንበት የኑሮ ደረጃ በ10 ብር መኖር አይቻልም። በ600 ብር በወር ትራንስፖርትህን፣ ምግብህን፣ የቤት ክራይህን፣ የዘይትህን፣ እና ሌሎች ነገሮችን ችለህ ከኖርክህ ትልቅ ነገር ነዉ። ስለዞህ በ20 ብር ቢሰላ፣ እሱም ደህነቱ 30 በመቶ የነበረዉ ወደ 60 በመቶ ያድጋል ማለት ነዉ። ሁለት እጥፍ ይሆናል ማለት ነዉ።>>


ደህነት የሚለካዉ በገቢ ምንጭ ብቻ ሰይሆን የተስተካከለ የትምህርት አቅርቦት እንዲሁም ጤናን ለመጠበቅ በመሳሰሉ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለመሆን አቅምም ሲኖር መሆኑን ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ተናግረዋል። መንግስት ከርዳታ እና ከዓመታዊ ገቢ የመገኘዉን ገንዘብ ማኅበረሰቡ ለትምህርት፣ ለጤና እና ሌሎች አገልግሎቶች ላይ በትክክል እንዲደርስ እንዳላደረገም ፕሮፊሰር አለማየሁ አመልክተዋል። ድኅነትን አስመልክቶ ባለፉት ቅርብ ጊዜያት ባደረጉት የጥናት መዘርዝር ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ፣ ከኬንያ እና ከታንዛያ በታች ትገኛለች። ይህን ችግር ለመቅረፍ መፍትሄ የሚሆነዉ ይላሉ አቶ አለማየሁ፣

<<ለኔ ይህ አንድ ፖሊሲ ነዉ። ፖሊስ ሲባል፣ በሁለት እንከፍለዋለን፣ የማይክሮ ኤኮኖሚ ፖሊስ የምንለዉ አለ፣ አጠቃላይ ኤኮኖሚን የሚመለከት ፖሊስ፣ ሁለተኛዉ ደግሞ ማይክሮ ኤኮኖሚ ፖሊስ የምንለዉ አለ፣ በየመስኩ ያለ፣ ለምሳሌ የእርሻ ፖሊስ ወይም የኢንዱስትሪ ፖሊስ፣ የትራንስፖርት ፖሊስ፣ የትምህርት ፖሊስ፣ የጤና ፖሊሲ የሚባሉት ማይክሮ ፖሊስ እንላቸዋለን ማለት ነዉ። እነሱ ጋር ችግር አለ ማለት ነዉ። ወይ የማይገባ ህንፃ ላይ ነዉ ያተኮርከዉ።ሰዉ ላይ አይደለም፣ እንደዚህ እንደዚህ አይነቱ ማለት ነዉ ማይክሮ ፖሊስ። ማይክሮ ፖሊስ ደግሞ የተረጋጋ ኤኮኖሚና ረጅም ጊዜ እቅድህ ለዉጥ የሚያመጣ ነዉ። ለምሳሌ ፋይናንስ የሚያደረጉት ትልልቅ ፕሮጄክቶችን ብር እያተምክ ከሆነ የገንዘብ ግሽበት ያመጠል፣ የገንዘብ ግሽበት ደግሞ መጀመርያዉኑ የሚያጠቃዉ ደኃዉን ነዉ ምክንያቱም ደኃዉ እስከ 70 በመቶ ገቢዉን ምግብ ላይ ነዉ የምያጠፋዉ፣ ምግብ ነዉ መጀመርያ የምወደደዉ ስለዚህ ይህ የማክሮ ኤኮኖሚ ፖሊስህ ስህተት ነዉ ማለት ነዉ፣ ወደ ድህነት ዉስጥ ይከተዋል ሰዉን። ብዙ ዶላር ሳይኖር፣ ወደ አገር ዉስጥ የማስገባት አቅም ሦስት ብሊዮን ሆኖ 12 ብሊዮን ወደ አገር የምታስገባ ከሆነ የሃገርህን የዉጭ ምንዛሪ አጠብቅም ማለት ነዉ። እሱ ደግሞ ገንዘብህን እያረከሰብህ ያመጣል፣ ብር ስረክስ ደግሞ የገንዘብ ግሽበት ይመጣል፣ ይህ እንግዲህ የማክሮ ኤኮኖሚ ችግር ነዉ። የግብርና ፖሊስ ላለፉት 24 ዓመታት አንድ በመቶ ነዉ የመስኖ ስራ የተሰራበት፣ ምንም አልተሰራበትም። ቢሰራበት ኖሮ የምግብ እጥረት ልታገኝ ትችላለህ፣ ዝናብ በጠፋ ቁጥር መለመን አያስፈልግም ነበር።>>

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic