የ2011 የዓለም የኤድስ ቀን ዘገባ | ዓለም | DW | 01.12.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የ2011 የዓለም የኤድስ ቀን ዘገባ

እ.ጎ.አ በ 2010 በኤድስ የሞቱትና ፣ HIV በደማቸው ውስጥ የተገኘ ሰዎች ቁጥር ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መሆኑን እ.ጎ.አ የ 2011 ዓ.ም የዓለም የኤድስ ዘገባ ያስረዳል ።

default

የኤድስ ህሙም በህከምና ላይ

የተባበሩት መንግስታት የኤድስ መከላከያ መርሃ ግብር በዚሁ ዓመት የHIVን ስርጭት ለመግታት በተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት መገኘቱን አመልክቷል ። ለዚህም ዘገባው በምክንያትነት ከጠቀሳቸው ውስጥ አንዱ ከሁሉም በተለይ አብዛኛዎቹ የ HIV ተጠቂዎች በሚገኙበት በአፍሪቃ ለኤድስ ህሙማንና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ሰዎች የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት መሻሻሉ ነው ። የዶቼቬለው Gudrun Heise ባለፈው ሰኞ ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ይፋ የሆነውን ይህን ዘገባ በአጭሩ ቃኝቶታል ።

30.11.2011 TT AIDS 2

እ.ጎ.አ የ 2011 የዓለም የኤድስ ዘገባ በጥቅሉ በዓለም ዙሪያ በ HIV የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ማብሰሩ እንደ አንድ በጎ ውጤት የሚታይ ነው ። ይሁንና አሁንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ በርካታ የችግሩ ተጠቂዎች ባሉባቸው ሃገራት ለኤድስ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ የበሽታው ስርጭትና የግንዛቤ እጥረት ማሳሰቡ አልቀረም ። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከመካከላቸው አንዳንዶች አነጋግሯል ። የባለሞያ አስተያየትም ጠይቋል ።

ሂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic