የ2008 አዲስ አመት ልዩ ዝግጅት | ኢትዮጵያ | DW | 12.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የ2008 አዲስ አመት ልዩ ዝግጅት

የኢትዮጵያ አዲስ አመት አከባበር በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ፤

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:40
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
05:40 ደቂቃ

የአዲስ ዓመት ዋዜማ

አዲሱ የኢትዮጵያውያን 2008 ዓመተ ምህረት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ዛሬ ተከብሯል። በዓሉ ከዋዜማው አንስቶ ምን ይመስል እንደነበር በዕለቱ የአንድ ሰዓት ልዩ ዝግጅት ቃኝተናል። በዓሉ በሚከበርበት ኢትዮጵያ ዋዜማው በአዲስ አበባ ምን ይመስል እንደነበር በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል። ሌላው በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢ ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር ደግሞ የጥቂት ኢትዮጵያውያን የአዲስ አመት ምኞት እና እቅዳቸውን አሰባስቧል።

ዓመት በዓል ሲደርስ ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ሞቅ ደመቅ ማድረጊያ፤ ዶሮ እና በግ መግዣ እያሉ ከሌላው ጊዜ በተለየ ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ይልካሉ። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ደግሞ ለአዲሱ ዓመት በኃዋላ የገንዘብ ማስተላለፊያ ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ሲልኩ ያገኛቸውን ኢትዮጵያውያን አነጋግሮ እንዲሁ ጥንቅር ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር

መክብብ ሸዋ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች