የ2008 ማብቂያ ክንዉኖች | ዓለም | DW | 22.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የ2008 ማብቂያ ክንዉኖች

ሰሞኑን ከኢራቅ እስከ አፍቃኒስታን፤ ከእስራኤል እስከ ፍልስጤም፣ ከሶማሊያ እስከ ዚምባቡዌ፣ ከአዉሮጳ እስከ አሜሪካ የተከናወኑት ብዙ ጉዳዮች በአሉ-ሳይደርስ አከባበሩን

default

ጫማዉ

የጎርጎሳዉያኑን የዘመን ቀመር የሚከተለዉ አለም በየአመቱ እንደሚያደርገዉ ሁሉ የክርስቶስን ልደት ሊያከብር፣ የፍቅር፣ ዉዴታ፣ አክብሮት፣ዉለታዉን መጠን በሚቀበል-በሚሰጠዉ ቁስ ሊሰፍር-ሊያሰፍር ሁለት ጀምበር ቀረዉ።በሰጠ-በተቀበለዉ፣ ባወጣ ባስገባዉ እንደቦርቀ ወይ እንዳዘነ አሮጌዉን አመት ይሰናበታል።የበአል-ዝግጅቱ፣ የስጦታ ቁሱ ሸመታ እንዴትነት፤ የዘመኑ ክንዉን ምንነት ብዙ ሲባልለት ሰሞኑን ከኢራቅ እስከ አፍቃኒስታን፤እስራኤል እስከ ፍልስጤም፣ ከሶማሊያ እስከ ዚምባቡዌ፣ ከአዉሮጳ እስከ አሜሪካ የተከናወኑት ብዙ ጉዳዮች በአሉ-ሳይደርስ አከባበሩን፤ አዲሱ ዘመን ሳይበርቅ ሒደቱን በያኝ መምሰላቸዉ አጠያያቂዉ።እንዴት ለምን ላፍታ አብረን እንቆይ።