የ2007 የኢትዮጵያ ምርጫ ሂደት ውጤትና የወደፊቱ ጉዞ | ኢትዮጵያ | DW | 31.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የ2007 የኢትዮጵያ ምርጫ ሂደት ውጤትና የወደፊቱ ጉዞ

በምርጫው ከተሳተፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋና ዋና የሚባሉት የምርጫውን ውጤትም ሆነ ሂደት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። የአፍሪቃ ህብረት ብቻ በውጭ ታዛቢነት የተካፈለበት የእሁዱ ብሔራዊ ምርጫ ሰላማዊ መሆኑ ቢነገርም ተቃዋሚዎች ፍትሃዊም ሰላማዊም አልነበረም ብለዋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 27:26
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
27:26 ደቂቃ

የ2007 የኢትዮጵያ ምርጫ ሂደት ውጤትና የኢትዮጵያ የወደፊት ጉዞዋ

5ተኛው የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ምርጫ ሂደትና ውጤት እንደቀደሙት ምርጫዎች እያነጋገረ ነው ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከትናንት በስተያ እንዳሳወቀው ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ በመጀመሪያው ደረጃ ውጤት መሠረት አብዛኛውን የፓርላማ መቀመጫ አግኝቷል ። ሙሉው ውጤት ባይነገርም በአሁኑ ምርጫ ተቃዋሚዎች ካለፈውም ምርጫ በባሰ ሁኔታ የተሸነፉ ይመስላል ። በምርጫው ከተሳተፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋና ዋና የሚባሉት የምርጫውን ውጤትም ሆነ ሂደት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል ።የአፍሪቃ ህብረት ብቻ በውጭ ታዛቢነት የተካፈለበት የእሁዱ ብሔራዊ ምርጫ ሰላማዊ መሆኑ ቢነገርም ተቃዋሚዎች ፍትሃዊም ሰላማዊም አልነበረም ብለዋል ።የየ2007 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ሂደት ውጤትና የወደፊት ጉዞ በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ ርዕስ ነው ።

ኂሩት መለሰ

ማንተፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic